Vehicle and machinery sale

ብርሃን ለሕፃናት ያገለገሉ 6 (ስድስት) የሞተር ሳይክሎች አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ብርሃን ለሕፃናት የማህበረሰብ ተሃድሶን መሰረት በማድረግ ሕፃናት ተኮርና የአካል ጉዳትን ያማከለ ሁለገብ አገልግሎት ለመስጠት እ.ኤ.ኢ በዲሴምበር 1997 የተቋቋመ ግብረ ሰናይ ድርጅት ነው፡፡

በመሆኑም ድርጅቱ በአዲስ አበባ ከተማ በቀድሞው ወረዳ 22 በጥቂት ቀበሌዎች የተጀመረው ሥራ ዛሬ ላይ በአምስት ክልሎች ማለትም በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ጭልጋ ወረዳ፣ በደቡብ ወሎ ደሴ ከተማና ኃይቅ፣ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በቢሾፍቱ ከተማና በአድአ ወረዳ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ በሃዲያ ዞን፣ በአፋር ክልላዊ መንግስት፣ በሲዳማ ክልል በሃዋሳ ከተማ እና በመልጋ ወረዳ ማህበረሰብን መሠረት ያደረጉ ፕሮግራሞችን ተግባራዊ በማድረግ ለአካል ጉዳተኛና በተለያዩ ምክንያቶች ለከፋ ችግር የተጋለጡ ሕፃናትን ለማብቃት የድርሻውን ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

ስለሆነም ድርጅታችን ብርሃን ለሕፃናት ያገለገሉ 6 (ስድስት) የሞተር ሳይክሎች አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሱና በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ፡-

1. በዘርፉ የታደሰ የሥራ (የንግድ ፈቃድ )ያላቸው፣

2. ከዘመኑ ግብር ዕዳ ነጻ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

3. የጨረታ ማስከበሪያ ከሚያቀርቡት ዋጋ አንድ ፐርሰንት (CPO) ማስያዝ የሚችሉ፣

ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች 100 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነድ ከታች ከተገለፀው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት በመውሰድ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ሞልተው ማቅረብ ይገባቸዋል፡፡

አድራሻ፡ ሜክሲኮ አደባባይ ከፖሊስ ሆስፒታል ጀርባ አልሳም የመኖሪያ መንደር ፊት ለፊት ከብስራት ሆቴል አጠገብ ብርሃን ለሕፃናት ህንፃ፣

ስልክ ቁጥር 011-554-48-14/45 092-272-09-20 እና 099-050-03-33 ያሳውቁን።

ብርሃን ለሕፃናት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-01
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት
  • Bid opening: 2026-08-01 17:00
  • Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን እና ሰዓት አልተገለጸም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Berhan For Children
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Jul 28, 2026)
  • Posted at: 2026-07-28T08:17:19.000Z
← Back to all tenders