የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር መሬት መምሪያ፡ የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
Description
የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ- አንቀፅ 1 መሰረት በ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር የከተማ መሬት በልዩ የሊዝ ጨረታ ለሆቴል/7/፣ ለሞልና አፓርታማ/10/ በድምሩ /17/አስራ ሰባት የሚሆኑ ቦታዎችን በልዩ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል።
በመሆኑም፡-
1. መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት ይህ ማስታወቂያ በአማራ ቴሌቪዥን ጨረታው እንደሚጀምር ከተነገረበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 አስር የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 2000/ሁለት ሺህ/ በመክፈል ቀበሌ 08 ከአዲሉ መሬት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 310 በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
2. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ የጨረታ ሰነድ መሸጥ ከጀመረበት ቀን አንስቶ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 11፡00 ሰዓት ብቻ በቢሮ ቁጥር 310 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ይሆናል።
3. ጨረታው የሚዘጋው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ይሆናል።
4. ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከጥዋቱ በ4፡00 ሰዓት ጀምሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሲሆን ጨረታው የሚከፈትበትን ቦታ በተመለከተ በውስጥ ማስታወቂያ የሚገለጽ ይሆናል።
5. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በመምሪያው የውስጥ ማስታወቂያ መለጠፊያ ሰሌዳ እና በBahirdar City Communication የፊስ ቡክ ገፅ ማግኘት ይቻላል።
6. መስሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር መሬት መምሪያ
ባህር ዳር
Tender details
- Deadline: 2026-05-21
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአማራ ቴሌቪዥን ጨረታው እንደሚጀምር ከተነገረበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-22 10:00
- Bid opening (note): ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከጥዋቱ በ4፡00 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር መሬት መምሪያ
- Bid document price: 2000.00 ብር
- Published: May 10, 2026
- Posted at: 2026-05-11T10:52:20.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.