ፀደይ ባንክ አ.ማ. የቦታዉ ስፋት 150 ካ.ሜ የሆነ መኖሪያ ቤት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
ፀደይ ባንክ አ.ማ. ለአርዲ የግንባታ እቃዎች ማምረቻ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ለሰጠዉ ብድር በመያዣ የያዘዉን በአዲስ አበባ ከተማ ልደታ ክ/ከተማ የሚገኘዉንና በአቶ አንዱዓለም የሽዋስ ዓለሙ የካርታ ቁጥር AA000030901020 የቦታዉ ስፋት 150 ካሜ መኖሪያ ቤት በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸዉ በፊት የሚከተሉትን ደምቦች በመገንዘብና ቅድመ ሁኔታዎችን በማሟላት ተጫራቾች እንዲጫረቱ ይጋብዛል።
- የቤቱ የጨረታ መነሻ ዋጋ ግምት 40,248,433.62 (አርባ ሚሊዮን ሁለት አርባ ስምንት ሺህ አራት መቶ ሰላሳ ሶስት ብር ከ62 ሳንቲም የሆነ
- ተጫራቾች የቤቱን ጨረታ መነሻ ዋጋ ብር ¼ (በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲ.ፒ.ኦ) በጸደይ ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታዉ አሸናፊ አሸናፊነቱ የሚረጋገጠዉ የጨረታዉ ዉጤት በሚመለከተዉ አካል ጸድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠዉ ብቻ ይሆናል።
- በጨረታዉ የሚሳተፈዉ በህግ ሰዉነት ያገኘ ከሆነ የድርጅቱ መመስረቻ ጽሁፍ ወይም መተዳደሪያ ደምብ፤ ህጋዊ ሰዉነት ያገኘበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ህጋዊ ዉክልና ማቅረብ አለበት።
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ10 ቀናት ዉስጥ አጠቃሎ መክፈልና በጫረታ ያሸነዉን ንብረት መረከብ ይኖርበታል። አሸናፊዉ በ10 ቀናት ዉስጥ ገንዘቡን ካልከፈለ ጨረታዉ ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘዉ ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።
- በጨረታዉ ለተሸነፉ ተጫራጮች ያስያዙት ጥሬ ገንዘብ ወይም ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል።
- የጨረታ አሸናፊዉ ከሚገዛዉ ንብረት ዋጋ በተጨማሪ ከቤቱ ጋር የተያያዙ ማናቸዉም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፡ ግብር፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ 15% እና ከስም ዝዉዉሩ ጋር የሚገናኙ ማንኛዉንም ወጭዎች ገዢ ይሸፍናል/ ይከፍላል። ዉዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሆኖ ለቀረዉና የክፍያ ጊዜዉ ላልደረሰ የሊዝ ክፍያ ገዢ ከሚመለከተዉ የመንግስት አካል ጋር እንዲዋዋል ይደረጋል።
- ተጫራቾች ቤቱን /ድርጅቱን/ በባንኩ አማካኝነት መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ።
- ከፍ ሲል የተጠቀሰዉን ንብረት ለሚገዛና የባንኩን የብድር ፖሊሲና መመሪያ መመዘኛዎች ለሚያሟላ ተጫራች በሚሰጠዉ ከፍተኛ ዋጋ ባንኩ እስከ 30% (ሰላሳ በመቶ) ብድር ሊያመቻች ይችላል።
- ጨረታዉ የሚካሄደዉ ሰኔ 1/2018 ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6:00 ሰዓት በአዲስ አበባ ከተማ በልደታ ክ/ከተማ ልዩ ቦታዉ ሰንጋ ተራ በባንኩ ዋና መ/ቤት 11ኛ ፎቅ ይሆናል።
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የጠተበቀ ነዉ።
ለተጨማሪ መረጃ፡- ፀደደ ባንክ ዋና መ/ቤት
በስ.ቁ +251 91 877 9825 ደዉሎ መጠየቅ ይቻላል።
Tender details
- Deadline: 2026-06-08
- Bid closing time: 12:00
- Bid opening: 2026-06-08 12:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Tsedey Bank S.C.
- Buyer address: Legahar Orda Building, 8th Floor room No-804
- Bid bond: 25%
- Published: May 10, 2026
- Posted at: 2026-05-11T12:13:38.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.