በአብክመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በሰንበቴ ከተማ አስተዳደር የሰንበቴ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የጠቅላላ ስፋት 615 ካሬ ሜትር የሆነ አንድ ቦታ ለሆቴል አገልግሎት ብቻ የሚውል በመደበኛ ጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ማስተላለፍ ይፈልጋል

Description

የመጀመሪያ ዙር የመሬት ሽያጭ
የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

በአብክመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በሰንበቴ ከተማ አስተዳደር የሰንበቴ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1፡ ከ ሀ እስክ ሠ በተዘረዘረው መሰረት በሰንበቴ ከተማ ውስጥ የጠቅላላ ስፋት 615 ካሬ ሜትር የሆነ አንድ ቦታ ለሆቴል አገልግሎት ብቻ የሚውል በመደበኛ ጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ማስተላለፍ ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመሳተፍ ፈቃደኛ የሆኑ ተጫራቾች ፡-

1.1 የጨረታውን ሰነድ በሰንበቴ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በመሬት ልማትና ማኔጅመንት ዋና የሥራ ሂደት ቢሮ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።

1.2 ተጫራቾች ቦታዎቹ የሚገኙበት ድረስ በመሄድ አጠቃላይ የቦታዎቹን ሁኔታ በማየት ዋጋ ማቅረብ ይችላሉ።

1.3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው ስፔስፊኬሽን /Specification/ መሰረት መሆን ይኖርበታል፣

1.4. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ጠቅላላ ቦታ ስፋት በሊዝ መነሻ ዋጋ ተባዝቶ ከሚገኘው ውጤት 5 በመቶ ያላነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ ክፍያ ማዘዣ/CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤ ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይንም ከ5 ከመቶ ቢያንስ ተጫራቹ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከውድድር ይሰረዛል።

1.5. ተጫራች የጨረታውን ሰነድ፣ ሲፒኦ እና ሌሎች የጨረታ ሰነዶችን በታሸገ ኤንቨሎፕ በአብክመ በኦብ ዞን በሰንበቴ ከተማ መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በመሬት ልማትና ማኔጅመንት ዋና የሥራ ሂደት ቢሮ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ከ3/9/2018 ዓ.ም እስከ 15/9/2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

1.6. ጨረታው የሚዘጋበት ቀን በ15/9/2018 ዓ.ም 11፡00 ሰዓት ይሆናል፣

1.7. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ18/9/2018 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት በሰንበቴ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ ቤት አዳራሽ ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

1.8. ቦታውን ለመጎበኘት ለሚፈልጉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት ለሽያጭ የተዘጋጁ ቦታዎች በሚገኙበት በሰንበቴ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በሚመድባቸው አስጎብኝዎች ቦታዎቹን መመልከት ይችላሉ።

1.9. የአካበቢውን ወቅታዊ የሊዝ ጨረታ መነሻ ዋጋ እና ሌሎች የከተማ መሬትን በሊዝ ለማስተዳደር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 721/2004 መሰረት በማድረግ በሰንበቴ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ መመልከት ይችላሉ።

1.10 መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች፡-033 118 0376 ወይም 09 31 96 91 82መጠየቅ ይችላሉ።
በአብክመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በሰንበቴ ከተማ አስተዳደር የሰንበቴ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-23
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid opening: 2026-05-26 10:00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Senbete City Administration City and Infrastructure Office
  • Bid bond: 5 በመቶ ያላነሰ
  • Bid document price: ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ብር 400.00
  • Published: May 12, 2026
  • Posted at: 2026-05-12T12:01:51.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders