የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ለመኖሪያ 14 (አስራ አራት) ቦታዎች፣ ለንግድ ድርጅት 67 (ስልሳ ሰባት)፣ የግብርና ምርት ማከማቻ መጋዘን 5 (አምስት) በመደበኛ ጨረታ እና ለልዩ ጨረታ የሚውል 1 (አንድ) ለሆቴል አገልግሎት የሚውል ቦታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል
Description
የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
1. የጨረታ ዙር፡- የ2018 በጀት ዓመት 3ኛ ዙር ጨረታ
2. የጨረታዉ ዓይነት፡- መደበኛ እና ልዩ ጨረታ
3. የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገዉ አዋጅ 721/2004 አንቀጽ 8 ጽ ንዑስ አንቀጽ 1 በፊደል ተራ ከሀ እስከ ሠ በተዘረዘረዉ መሰረት ለመኖሪያ 14 (አስራ አራት) ቦታዎች፣ ለንግድ ድርጅት 67 (ስልሳ ሰባት)፣ የግብርና ምርት ማከማቻ መጋዘን 5 (አምስት) በመደበኛ ጨረታ እና ለልዩ ጨረታ የሚውል 1 (አንድ) ለሆቴል አገልግሎት የሚውል ቦታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል። በመሆኑም መጫረት የሚፈልጉ ማንኛዉም 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ እድሜ ያለው ኢትዮጵያዊ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ግንቦት 03/2018 ዓ.ም ጀምሮ በተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ የቦታዉን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ለመኖሪያ ብር 500 (አስት መቶ ብር) ለንግድ ድርጅት ብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር)፣ ለመጋዘን ብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል በእን/ከ/አስ/መ/ጽ/ቤት ከ/መ/ማ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 004 ዘወትር በሥራ ቀን እስከ 11፡00 መግዛት ይችላሉ።
4. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ሰነዱን ከገዙበት ቀን ጀምሮ እስከ ሚዘጋበት ቀን ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 11፡00 ብቻ ይሆናል።
5. ጨረታዉ የሚዘጋዉ ሰነድ ሽያጭ ባለቀበት ቀን ከቀኑ 11፡00 ይሆናል።
6. ለጨረታ የቀረቡ ቦታዎችን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን በኋላ ከተቋሙ የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚወጣው ፕሮግራም መሰረት ከባለሙያ ጋር መጐብኘት ይችላሉ።
7. የመኖሪያ ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው ከታሸገበት በቀጣዩ የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሲሆን በቀጣዩ የስራ ቀን ደግሞ የድርጅት በእን/ከ/አስተዳደር ከንቲባ አዳራሽ ይከፈታል።
8. ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከተቋሙ የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ እና በስልክ ቁጥር 058 227 0005 ደውለው መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
9. መስሪያ ቤቱ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
የእንጅባራ ከተማ አስተዳድር መ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-05-21
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ግንቦት 03/2018 ዓ.ም ጀምሮ በተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ከቀኑ 11፡00
- Bid opening: 2026-05-22 12:00
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
- Region: Amhara
- Publishing entity: Injebara City Administration Urban Infrastructure Development Bureau
- Bid document price: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Published: May 11, 2026
- Posted at: 2026-05-12T12:19:25.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.