የሸዋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ከተማና መሠረተ ልማት ጽ/ቤት ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች ማለትም ለንግድ አገልግሎት እና ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውሉ ቦታዎችን በግልፅ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል

Description

የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

1. የጨረታ ዙር........18ኛ

2. የጨረታ አይነት.......መደበኛ

3. የሸዋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ከተማና መሠረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማን ቦታ በሊዝ ስለመያዝ የሚደነግገው አዋጅ 721/2004 አንቀፅ ንኡስ አንቀፅ 1 ይህንኑ አዋጅ ለማስፈፀም የአብክመ ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ የከተማን ቦታ በሊዝ ስለመያዝ ባወጣው ደንብ ቁጥር 103/2004 በክፍል 3 በአንቀፅ 10 በንኡስ አንቀፅ 1 በፊደል ተራ ከ "ሀ" እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች ማለትም ለንግድ አገልግሎት ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውሉ ቦታዎችን በግልፅ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፤

በመሆኑም መጫረት የሚፈልግ ግለሰብ ወይም ድርጅት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የቦታው ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል በሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 24 ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት የሚቻል መሆኑን እናሳውቃለን።

4. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው መሰረት መሆን ይኖርበታል።

5. ተጫራቾች ሁለት የተለያየ ፖስታዎችን በማዘጋጀት ከገዙት ጨረታ ሰነድ ውስጥ በመለየት ክፍል ሁለት የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን እና ክፍል 3 የጨረታ ሃሳብ ማቅረቢያ ሰነዱን እንዲሁም ሲፒኦን ሁለቱን ሰነዶች አንዳንድ ኮፒ በማድረግ ኦርጅናሉን ለብቻ ኮፒውን ለብቻ በተለያዩ ፖስታዎች በሰም ወይም በአካባቢው በሚገኝ ማጣበቂያ በማሸግ እና ፖስታዎቹ ላይ ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት ለይቶ በመፃፍ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከ05/09/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለአስር ተከታታይ የስራ ቀናት ፖስታውን እስከ 10ኛው ቀን 11 ሰዓት ማለትም 18/09/2018 ዓ.ም በከተማ አስተዳደሩ ለጨረታ ተግባር በተዘጋጀው ቦታ ኦርጅናሉን ሰነድ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እና ኮፒውን ሰነድ ደግሞ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባችሁ።

6. ጨረታው የሚዘጋው ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት 05/09/2018 ዓ.ም በ10ኛ /በአስረኛው/ የስራ ቀን 18/9/2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ ይሆናል።

7. የጨረታ መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ በሶስት ሰዓት ላይ ይከፈታል።

8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ከተማና መሠረተ ልማት ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው ቦታ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አወጣበት ቀን ጀምሮ 11ኛው/አስራ አንደኛው /የስራ ቀን 19/09/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጨረታው ይከፈታል።

9. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በጨረታ ሰነዱ ላይ እና በጽ/ቤቱ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ እንዲሁም የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 21 ላይ ማግኘት ይችላሉ።

10. መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ቦታውን መጎብኘት ለሚፈልጉ ተጫራቾች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገለጸው መርሃ ግብር መሰረት የምናስጎበኝ ይሆናል።

በአብክመ በሰ/ሸዋ ዞን በሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር


Tender details

  • Deadline: 2026-05-26
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid opening: 2026-05-27 09:00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Shewa Robit City Administration City Infrastructure Development office
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published: May 13, 2026
  • Posted at: 2026-05-13T09:30:21.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders