ራክሮብ ቢዝነስ ኃ. የተ. የግል ማህበር ሱቆቹን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል
Description
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ
መለያ ቁጥር: RAC/01/2018
ራክሮብ ቢዝነስ ኃ. የተ. የግል ማህበር በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ጎርጎርዮስ አደባባይ አጠገብ በገነባቸው ሱቆች ውስጥ በኤሌክትሮሜካኒካል፣ በኤሌክትሪካል፤ ሶላር ፓወር፤ በኬሚካል፣ ኮንስትራክሽን ማሺነሪዎችና መለዋወጫ ዕቃዎች እንዲሁም ተዛማጅ በሆኑ የንግድ ሥራ ዘርፍ ብቻ ላይ ለሚሰማሩ ተጫራቾች ሱቆቹን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል። በዚህም መሠረት ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- ተጫራቾች ሊከራዩ በመረጡት ሱቅ በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ VAT Registration Certificate፤ እና የቲን ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 03 ጎርጎሪዮስ አደበባይ አጠገብ የኦሮሚያ ባንከ ከሚገኝበት ህንጻ 2ኛ ፎቅ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚጫረቱባቸው ሱቆች ለየብቻ የአንድ ወር የኪራይ ዋጋ ቫትን ጨምሮ አሥር በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በራክሮብ ቢዝነስ ኃ. የተ. የግል ማህበር ስም አሰርተው ድርጅቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በታሸገ ፖስታ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ሱቆች የዋጋ ማቅረቢያ (financial) ሠነድ ኦሪጂናል እና አንድ ኮፒ ለየብቻ ተለይቶ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከላይ በተራ ቁጥር 2 በተጠቀሰው አድራሻ ቢሮ ቁጥር 1263/201 በመምጣት ድርጅቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ11ኛው የሥራ ቀን ልክ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዕለቱ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል። አስራ አንደኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ጨረታው ይከፈታል።
- የጨረታ አሸናፊዎች ማሸነፋቸው በጽሁፍ የሚገለጽላቸው እና የውል ስምምነት የሚፈፅሙ ይሆናል።
- በጨረታ ያላሸነፉ ድርጅቶች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡-ስልክ ቁጥር 09 40 41 41 41፣ 09 40 42 42 42፣ 09 87 43 43 43
አድራሻ፡-
አዲስ አበባ ወሎ ሰፈር ጎርጎርዮስ አደባባይ አጠገብ የኦሮሚያ ባንክ በሚገኝበት ህንጻ 2ኛ ፎቅ፣
ራክሮብ ቢዝነስ ኃ. የተ. የግል ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-05-23
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ11ኛው የሥራ ቀን ልክ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-23 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ11ኛው የሥራ ቀን ልክ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: ራክሮብ ቢዝነስ ኃ. የተ. የግል ማኅበር
- Bid bond: 10%
- Published: May 13, 2026
- Posted at: 2026-05-13T11:44:53.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.