ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በሰሚት በተለምዶ ፍየል ቤት ተብሎ በሚጠራ አካባቢ የሚገኙትን G+4 ህንፃ ጠቅላላ ቦታ ስፋት 750ካ.ሜ እና G+2 ህንጻ ጠቅላላ ቦታ ስፋት 442ካ.ሜ ያላቸው ህንፃዎችን ባሉበት ሁኔታ ለተለያዩ አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል
Description
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር: ኢኢግ/ግቢዴ/ብግጨ/004/2018
ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በሰሚት በተለምዶ ፍየል ቤት ተብሎ በሚጠራ አካባቢ የሚገኙትን G+4 ህንፃ ጠቅላላ ቦታ ስፋት 750ካ.ሜ እና G+2 ህንጻ ጠቅላላ ቦታ ስፋት 442ካ.ሜ ያላቸው ህንፃዎችን ባሉበት ሁኔታ ለተለያዩ አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
1. በዘርፉ የተሰማሩበት የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፣
2. የተጨማሪ ዕሴት ታክስ(ቫት) ወይም የቲኦቲ ተመዝጋቢ ፍቃድ፣
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣
4. የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፤
5. ተጫራቹ የሀገር ውስጥ፣ የዓለም አቀፍ ለትርፍ ያልተቋቋመ የእርዳታ ድርጅት (NGO) ወይም የሲቪክ ማህበራት ከሆነ ህጋዊ ሰውነት ያለው ማረጋገጫ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል።
6. ተጫራቹ ኢንቨስተር ከሆነ የኢንቨስትመንት ፈቃድ፣ የንግድ ማኅበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሑፍ፣ የሙያ አገልግሎት ሰጪ ከሆነ የሙያ ፍቃዱን ፎቶ ኮፒ ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል።
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ አዲስ አበባ ሜክሲኮ በሚገኘው የግሩፑ ዋና መስሪያ ቤት ብሎክ “C” የግብይትና ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት መምሪያ በመቅረብ የማይመለስ ብር 500 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሜክሲኮ ቅርንጫፍ በኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ስም በተከፈተው የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000028606177 በመክፈል እና የክፍያ ደረሰኙን በማቅረብ ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ መውሰድ ይችላሉ።
|
የሎት ቁጥር |
የሎት መጠሪያ ስም |
የሰነድ መሸጫ ዋጋ ብር |
የጨረታ ማስከበሪያ ብር |
|
ሎት 1
|
ለሆቴል፣ ለሆስፒታልና ክሊኒክ ፣ ባንክና ኢንሹራንስ፣ ለሱፐር ማርኬት፣ ለዘመናዊ ቢሮዎች፣ ለካፌና ሬስቶራንት ለትምህርት ቤት፣ ለገስት ሃውስ፤ ለመኖሪያ ቤት፤ ለተለያዩ ምርት ማሳያዎች እንዲሁም ለመሳሰሉት አገልግሎቶች |
500
|
50,000.00
|
|
ሎት 2
|
ለሆስፒታልና ክሊኒክ ፣ ለዘመናዊ ቢሮዎች፣ ለካፌና ሬስቶራንት፤ ለትምህርት ቤት፣ ለገስት ሃውስ፤ ለመኖሪያ ቤት እንዲሁም ለመሳሰሉት አገልግሎቶች |
500
|
50,000.00
|
8. ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበውን ሰነድ የኪራይ ዋጋ በግልፅ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ቴክኒካል ኦርጂናልና ኮፒ እና ፋይናሽያል ኦርጂናልና ኮፒ ለየብቻቸው ማስገባት አለበት።
9. ተጫራቾች የተጠቀሱትን ሰነድች በመግዛት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ህንፃዎቹን መመልከት ይችላሉ።
10. ጨረታው ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 8፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል። የጨረታው መክፈቻ ቀን በዓል ቀን ወይም ቅዳሜና እሁድ ላይ ከዋለ በቀጣይ ቀን የሚከፈት ይሆናል። ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር ጨረታውን ከመከፈት አይስተጓጎልም።
11. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራች አሸናፊነቱ በተገለፀ ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ቀርበው መዋዋል ይኖርባቸዋል። ሆኖም ውሉን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ ተዋውሎ ካልጨረሰ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለግሩፑ ገቢ ይደረጋል።
12. ግሩፑ ባወጣው ጨረታ ሰነድ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይሆናል።
13. ግሩፑ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ
በስልክ ቁጥር +251 98 633 3388 ወይም +251 98 633 3344 ደውሎ መጠየቅ ይችላል።
ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ
Tender details
- Deadline: 2026-06-01
- Bid closing time: 14:30
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 8፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-06-01 15:00
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 9፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ (ኢኢግ)
- Bid bond: 50,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Bid document price: 500.00 ብር በየሎቱ
- Published: May 14, 2026
- Posted at: 2026-05-14T07:09:26.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.