Stationery and office consumables
የደ/ኢት/ክ/መ ፕላንና ልማት ቢሮ ለ2018 በጀት ዓመት ለቢሮው አገልግሎት የሚውሉ አላቂ ዕቃዎች፣ ሌሎች አላቂ ዕቃዎች፣ የፅዳት ዕቃዎችና ኤሌክትሮኒክሶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የደ/ኢት/ክ/መ ፕላንና ልማት ቢሮ ለ2018 በጀት ዓመት ለቢሮው አገልግሎት የሚውሉ አላቂ ዕቃዎች፣ ሌሎች አላቂ ዕቃዎች፣ የፅዳት ዕቃዎችና ኤሌክትሮኒክሶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሠረት ተጫራቾች፡-
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥርና ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢየሆኑ እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል በተጨማሪ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ሊኖራቸው ይገባል።
- የጨረታ ማስከበሪያ ከሕጋዊ ባንክ CPO ወይም በካሽ ለ10,000 ከሚያቀርቡት ከዕቃ ጋር በተናጥል ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ሰነድ ስማቸውን ፊርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈር የድርጅቱን ማህተም መምታት ያለባቸው ሲሆን በጨረታው ሰነድ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን እና ሌሎች ተፈላጊ መረጃዎች በአንድ ኢንቨሎፕ በማሸግ ማለትም 1 ኦርጅናል 1 ኮፒ በመለያየት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ የደ/ኢት/ክ/መ ፕላንና ልማት ቢሮ እንደኛ ፎቅ ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት ላይ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይጠበቅበታል።
- ይህ ጨረታ አየር ላይ የሚቆየው ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 05 ቀናት ሲሆን ጨረታው በ 6ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ሰዓት ላይ የደ/ኢት/ክ/መ ፕላንና ልማት ቢሮ ተጫራቾች ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል።
- ተጫራቾች ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አይታገድም።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የሕዝብ በዓል ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈተው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት እና ቦታ ይሆናል።
- ይህ የጨረታ ዋጋ ለ45 የሥራ ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል የደ ኢት/ክ/መ ፕላንና ልማት ቢሮ ግ/ፋ/ን/አስ/ዳይፊክቶሬት ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡ 046 180 2396/ 046 180 4910
የደ/ኢት/ክ/መ ፕላንና ልማት ቢሮ
Tender details
- Deadline: 2026-05-19
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ጨረታ አየር ላይ የሚቆየው ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ6ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-19 12:00
- Bid opening (note): ይህ ጨረታ አየር ላይ የሚቆየው ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ6ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት
- Region: South Ethiopia Regional State
- Publishing entity: የደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ ፕላንና ልማት ቢሮ
- Bid bond: 10,000.00 ብር
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (May 14, 2026)
- Posted at: 2026-05-14T07:28:52.000Z