የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ /ባለመብት መኩ ጌታቸው እና በፍ/ባለዕዳ ሀና ሞገስ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌ/ከ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.325814 በ25/04/2017ዓ.ም እና የፌ/ከ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.325814 በቀን 07/04/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በፍ/ባለዕዳ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ በሸገር ከተማ አስተዳደር በለገጣፎ ለገዳዲ ክ/ከተማ ውስጥ የሚገኝ በካርታ ቁጥር L/X/L/D/37/00 የቦታ ስፋት በካርታ ላይ 140 ካ/ሜ ሲሆን በልኬት አጠቃላይ የቦታ ስፋት 170 ካ/ሜ የሐራጅ መነሻ 6,741,658.47 (ስድስት ሚሊዮን ሰባት መቶ አርባ አንድ ሺህ ስድስት መቶ ሃምሳ ስምንት ከ47/100) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሰኔ 9 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ5:00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ _ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ C.PO የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለስብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤጽ/ስም C.PO አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዞወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-16
  • Bid closing time: 11:00
  • Bid opening: 2026-06-16 11:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት
  • Bid bond: 25%
  • Published: May 14, 2026
  • Posted at: 2026-05-14T08:25:35.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders