ድጋሚ የወጣ የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት እነ አበባ ዋለልኝ እና የፍ/ባለዕዳ እነ መዳህኒት ዋለልኝ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/273778 በ19/05/2017 ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ እና በኮ/መ/ቁ/335656 በ14/08/2017 ዓ/ም በ02/06/2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአዲስ ክ/ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 07 የቤት ቁጥር 704 ይዞታው ሰነድ አልባ (መብት ያልተፈጠረለት) ማህደሩ በአቶ ዋለልኝ አይናለም ስም የተደራጀለት ይዞታው ንፅፅር(ፕሮፖርሽን) ሲሆን ጠቅላላ የቦታ ስፋቱ በ1988 አየር ካርታ መሰረት ጠቅላላ የቦታ ስፋት 1263.71 ካ/ሜ ሲሆን በዚህ ይዞታ ውስጥ ፍርድ ያረፈበት የቤት ቁጥር 704 የአንዱ ክፍል ቤት ስፋት 14.06 ካ/ሜ ግምት 1,431,931 25 (አንድ ሚሊዮን አራት መቶ አስራ ሦስት ሽህ ዘጠኝ መቶ ሰላሳ አንድ ብር 25/100) ከአንድ ከፍሉ ውጭ ያሉት ክፍሎች ስፋት 36.65 ካ/ሜ ግምቱ 3,733,027.31 (ሦስት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሰላሳ ሦስት ሽህ ሀያ ሰባት ብር 31/100) አጠቃላይ የቤት ቁጥር 704 ቤት ስፋት 50.71 ካ/ሜ የቤቱ ሽያጭ ዋጋ መነሻ ግምት 5,164,958.56 (አምስት ሚሊዮን አንድ መቶ ስልሳ አራት ሽህ ዘጠኝ መቶ ሃምሳ ስምንት ብር 56/100) ከቤቱ ላይ 5.25 ካ/ሜ መንገድ ጥናት ይነካዋል። የትራንዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መጋቢት 23 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ የተያዘ ቢሆንም በዕለቱ ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል። ስለሆነም በፌ/ከ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.335656 በቀን 13/8/2018 ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ድጋሚ ሐራጅ ጨረታ ሆኖ 1/4ኛ 1,291,239.64 (አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ዘጠና አንድ ሺህ ሁለት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ከ64/100) ሆኖ የትራዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውስድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-18
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-06-18 10:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published: May 16, 2026
- Posted at: 2026-05-16T07:36:41.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.