የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ በመደበኛ በጀት የቢሮ አገልግሎት የሚውል የፋየርወል እና የግቢ ፅዳት አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ በመደበኛ በጀት የቢሮ አገልግሎት የሚውል
1. የፋየርወል እና
2. 2019 ዓ.ም በጀት አመት የሚውል የግቢ ፅዳት አገልግሎት ናቸው በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች፡-
1. በሚወዳደሩበት ዘርፍ በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው
3. የግዥው መጠን ብር ከ200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ መሆን አለባቸው።
4. ጨረታው አዲስ ዘመን ጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀናት ጀምሮ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሰውን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
6. የግዥ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ/Specification/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል። ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400/አራት መቶ ብር/ በመክፈል ከገንዘብ ያዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 13 የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ። ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/BD BOND/ ለሚወዳደሩበት ግዥ ዓይነት ጠቅላላ ዋጋ የፋየርወል ዕቃ 200,000.00/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና፣ የግቢ ፅዳት አገልግሎት ግዥ ብር 10,000.00/አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው። ጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮ ህጋዊ ደረሰኝ ኮፒ በማድረግ ማቅረብ አለበት።
7. የጨረታ ሰነድ ተሞልቶ ከጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ ጋር ተያይዞ በፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የሞሉትን የግዥ ዓይነት በመጥቀስ ግልጽ ጨረታ የሚል ተፅፎበት ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት እና በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን መግባት ይኖርበታል።
8. ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአብክመ ትምህርት ቢሮ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ክፍል ጨረታው ይከፈታል።
9. የቢሮ የግቢ ፅዳት አገልግሎት አንድ የመልካም ስራ አፈፃፀም ማቅርብ የሚችል።
10. የጨረታ መክፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
11. ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ አብክመ ትምህርት ቢሮ በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል በግንባር በመቅረብ በፋክስ ቁጥር 058 222 0814 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 6267/ 058 320 9939 በመደወል ማግኘትይቻላል።
12. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የአማራ ብሔራዊ ክልላው መንግስት ትምህርት ቢሮ
Tender details
- Deadline: 2026-06-01
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡00
- Bid opening: 2026-06-01 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡30
- Region: Amhara
- Publishing entity: አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 400.00 /አራት መቶ ብር/ ለእያንዳንዱ ሎት
- Published: May 16, 2026
- Posted at: 2026-05-16T08:11:33.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.