በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ጉምሩክ ኮሚሽን የሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ለአገልግሎት የማይጠቀምባቸው የተለያዩ ኤሲዎች፣ ጀኔሬተር፣ ፍሪጅ፣ እስካነር፣ ፕሪንተር፣ የውሃ ሮቶ እና ሌሎችም በግልፅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በሰማራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ለአገልግሎት የማይጠቀምበት የተለያዩ ኤሲዎች፤ ፍሪጅ፣ እስካነር ፕሪንተር፣ የውሃ ሮቶ እና ሌሎችም በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር፡ CCSE Branch/001/2018
|
የጨረታ ቁጥር |
የጨረታው ሰነድ ሽያጭ የሚጀምርበት ቀን |
የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት |
የጨረታው መክፈቻ ቀን እና ሰዓት |
|
CCSE-Branch /001/2018 |
ግንቦት 08 ቀን 2018 |
ግንቦት 17 ቀን 2018 ከጠዋቱ 4:00 |
ግንቦት 17 ቀን 2018 ከጠዋቱ 4:15 |
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ጉምሩክ ኮሚሽን የሰመራ ጉ ቅ/ጽ/ቤት ለአገልግሎት የማይጠቀምባቸው የተለያዩ ኤሲዎች ጀኔሬተር ፍሪጅ፤እስካነር ፕሪንተር፣የውሃ ሮቶ እና ሌሎችም በግልፅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ድርጅት ወይም ግለሰብ ተጫራች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርቦ መወዳደር ይችላል።
1. በጨረታ ሽያጭ ስርዓት ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራች በዘርፉ የፀና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጠዋት 1፡00-6፡00 እና ከሰዓት 9፡00-12፡00 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋት 1፡00-5፡00 የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) ብር በመከፈል በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በመገኘት ይህ ጨረታ በማስታወቂያ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በግዥና ፋይናንሰ ቢሮ በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላል።
3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና CPO 50,000 (ሃምሳ ሺህ) ብር በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት (ETHIOPIAN CUSTOMS COMMSSON SEMERA OFFICE) ስም በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
4. ጨረታው ግንቦት 08 ቀን 2018 እስከ ግንቦት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ተከታታይ ለ10 ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ይሆናል፡፡ ጨረታ የሚካሄድበት ቦታ በሠመራ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አዳራሽ ቢሮ ሲሆን ጨረታው ግንቦት 17 ቀን 2018 ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
5. የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታ ማስታወቂያው ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ እስከ 16/09/2018 ዓ.ም ሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ነው።
6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተመላሽ የሚደረገው ላሸነፈበት ዕቃ ሙሉ ክፍያ ከፈጸመ እና የተከፈለበት ዕቃ ሙሉ በሙሉ ማንሳቱ ከተረጋገጠ በኋላ ነው፡፡እንዲሁም ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ውጤት በተገለጸ በሦስት (3) ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
7. አሽናፊው ተጫራች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በሦስት(03) ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን እቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ያለበት ሲሆን ይህንን ባይፈጽም ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ዋስትና ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ተደርጎ እቃው በድጋሚ ለጨረታ የሚቀርብ ሲሆን ነገር ግን የእቃውን ዋጋ ገቢ አድርጎ እስከ 1 ወር ጊዜ ውስጥ እቃውን ያላነሳ እንደሆነ ለሚቆይበት ተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ የሚከፍል ይሆናል፡ሆኖም እቃውን ከወር በላይ ከቆየ ለንብረቱ የከፈለው ዋጋ ለመስሪያቤቱ ገቢ ሆኖ እቃው እንደተተወ ተቆጥሮ በሽያጭ ይወገዳል።
8. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይንም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
9. ተጫራቾች ተመሳሳይ ዋጋ ቢያቀርቡ ቃለ ጉባኤ በመያዝ በእጣ የምንለይ መሆኑን እናሳውቃለን።
10. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ የተሰጠውን ዋጋ መለወጥ ማሻሻል ወይም ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይቻልም።
11. በጨረታ ለሚሸጥ ዕቃ የጨረታው ውጤት በደብዳቤ እንደተገለፀ ከአሸናፊው ጋር የሸያጭ ውል እንደተደረገ ይቆጠራል።
12. አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎቹን ባሉበት ሁኔታ በመረከብ ለመረከብ እና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ማንኛውንም ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይችላል።
13. ቅ/ጽ/ቤቱ ለጨረታ የቀረበውን እቃ ብዛት ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ ሙሉ መብት አለው።
14. ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃዳቸውን የሚገዙበት ዋጋ ቫትን (VAT) ጨምረው በዋጋ ማስገቢያ ቅፅ ላይ በመሙላት እና የጨረታ ማስከበሪያ ሰነዱን(CPO) በማካተት በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻቸው እና የጨረታ ማስከበሪያ ሰነዱን(CPO) በማካተት በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻቸውን እና የጨረታ ቁጥሩን በመጥቀስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን እስከ ግንቦት 16 ቀን 2018 ጠዋት ከ4፡ 00 በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ለተጨማሪ መረጃ ስ.ቁ: 033 366 1567/0912 344 883/0941 826 387
ጉምሩክ ኮሚሽን የሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-05-25
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-05-25 10:15
- Region: Afar
- Publishing entity: Ethiopian Customs Commission
- Buyer address: በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው የአማራ ህንጻ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published: May 16, 2026
- Posted at: 2026-05-16T08:40:58.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.