ስፋቱ 250 ካ.ሜ. በሆነ ቦታ ላይ ያረፈ የመኖሪያ ቤት ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

ለፍ/ቤታችን የህግ ኦፊሰር አቶ ደራራ ኢንሳርሙ ለመልካ ኖኖ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት
ለሳጅን ሽብሩ ቶሌራ
ባሉበት

በፍርድ ባለመብት ሙስጠፋ ሙሐመድ እና የፍርድ ባለዕዳ አዬቱ ኃይሌ መካከል ያለውን የአፈጻጸም ክርክር አስመልክቶ፤በዱከም ክ/ከተማ፣ መልካ ወረዳ ውስጥ የሚገኘው ስፋቱ 306 ካ.ሜ የሆነ፣ የቀድሞ ባለቤትነት ማረጋገጫ ወይም ካርታ ቁ. BMD-11933/ B/20/G-02-5436/00 የተሰጠበት ቀን 11/12/2015 ዓ.ም የሆነው በፍርድ ባለዕዳ አዬቱ ኃይሌ ስም ተመዝግቦ የነበረው፤ በአሁኑ ወቅት በካዳስተር ካርታ ቁ. BMD-1933B/016፣ ስፋቱ 250 ካ.ሜ. በሆነው ቦታ ላይ ያረፈው የመኖሪያ ቤት በጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 943,810.29 (ዘጠኝ መቶ አርባ ሶስት ሺህ ስምንት መቶ አስር ብር ከ29/100) ስለሚሸጥ ለአንድ ወር ያህል አየር ላይ ውሎ፤ ንብረቱን መግዛት የሚፈልግ ወገን በ11/10/2018 ዓ.ም ከ3፡00 እስከ 6፡30 ድረስ በሚካሄደው ግልጽ ጨረታ ስለሚሸጥ፤ ማንኛውም ተወዳዳሪ 1/4ኛ የጨረታውን መነሻ ዋጋ በሲፒኦ በቢሾፍቱ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት ስም በማስያዝ እንዲገዙ በማድረግ ኮሚቴው በታዘዘው አግባብ ሸጦ ውጤቱን ለ12/10/2018 ዓ.ም ረፋድ 4፡00 እንድታቀርቡ የቢሾፍቱ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት ጋብዟል።

የቢሾፍቱ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-18
  • Bid closing time: 12:30
  • Bid opening: 2026-06-18 12:30
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: የቢሾፍቱ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት
  • Bid bond: 25%
  • Published: May 17, 2026
  • Posted at: 2026-05-18T08:53:37.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders