አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ./ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ የሰጠው ብድር ባለመክፈሉ በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) 216/92 መሠረት በእዳ ማካካሻት የወረሳቸውን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋውን 1/4(አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው ለመሳተፍ ይችላሉ።
- ስለጨረታው አካሄድ እና ንብረቶች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን ሰነድ ንብረቶቹ በሚገኙበት የባንኩ ቅርንጫፎችና እና ስሜን ሆቴል አጠገብ በሚገኘው የባንኩ ሕንጻ የተወረሱ ንብረቶች አስተዳደር 6ኛ ፎቅ በመቅረብ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መውሰድ ይቻላል።
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት/ንብረቶች መረከብ ይኖርበታል። በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል። በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል።
- ተጫራቾች ንብረቱን ለመግዛት የሚሰጡትን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ላይ በተያያዘው የዋጋ ማቅረቢያ ቅፁ ላይ ካሰፈሩ በኋላ የጨረታ ማስከበሪያና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን በማያያዝ በስም በታሸገ ፖስታ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ጨረታው መካሄጃ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ጨረታው በሚካሄድበቸው ቦታዎች ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ አስመዝግበው ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከታች በሰንጠረዥ በተገለጸው ቦታ ሰኔ 9 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 አስከ 5፡30 ይካሄዳል።
- የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን፣ ግብር፣ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጪዎች ገዢ ይከፍላል። የሊዝ ክፍያ ውል ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል።
- ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አሲዞ መጎብኘት ወይም ማየት ይቻላል።
- በባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟሉ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢዎች ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-126-4594 / 09 18-77 84 27 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፤
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪው ሙሉ ስም |
የመያዣ ሰጭው ስም |
የንብረቱ ዓይነትና አገልግሎት |
የቦታው ስፋት |
የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር |
ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ |
የጨረታ መነሻ ዋጋ |
ጨረታው የወጣበት ጊዜ |
ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ |
|
1 |
ሲትረስ ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ |
መስከረም ታደሰ |
የንግድ ቤት |
2600 ካ.ሜ |
715/97 |
ኦሮሚያ ብ/ክ/መ ሰንዳፋ በኬ ከተማ |
9,998,261.35 |
በድጋሚ |
ሰኔ 9 ቀን 2018 ዓ.ም አ.አ ከተማ ሰሜን ሆቴል ጎን በሚገኘው የባንኩ ህንጻ 6ኛ ፎቅ እና ንብረቶቹ በሚገኙበት ዲስትሪክት ጽ/ቤቶች |
|
2 |
ጂዲ ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ ኃ/የተ/ የግ/ማ |
ደጀኔ ሞገስ |
መኖሪያ ቤት |
302 ካ.ሜ |
የካ/188838/07 |
አ.አ ከተማ የካ ክ/ከ ወረዳ 13 |
28,102,022.43 |
በድጋሚ |
“ |
|
3 |
ቢንያም አየለ |
ተበዳሪው |
ኮንዶሚኒየም |
70.75 ካ.ሜ |
AA00005 1305559142 |
አዲስ አበባ የካ ወ.13 |
5,157,628.56 |
ለመጀመሪያ ጊዜ |
“ |
|
4 |
ክንዱ አለበል |
ተበዳሪው |
መጋዘን |
5000 ካ.ሜ |
262/2008 |
አማራ ብ/ክ/መ ገንደውሃ ከተማ |
12,528,675.00 |
በድጋሚ |
“ |
|
5 |
ወይ. የሰውዘር አዝመራው |
ተበዳሪው |
መኖሪያ ቤት |
250 ካ.ሜ |
1686/2008 |
አማራ ብ/ክ/መ ሞጣ ከተማ |
1,152,510.00 |
በድጋሚ |
“ |
|
6 |
እስክንድር አስራት |
ተበዳሪው |
መኖሪያ ቤት |
150 ካ.ሜ |
ከገ/112206/12 |
አማራ ብ/ክ/መ አዴት ከተማ |
943,662.13 |
በድጋሚ |
“ |
|
7 |
ኢብራሂም መሀሐመድ ኑር |
ይድነቃቸው መንበሩ |
ሆቴል |
820 ካ.ሜ |
804/07 |
ኦሮሚያ ብ/ክ/መ ኦለንጭቲ ከተማ |
16,662,424.75 |
በድጋሚ |
“ |
|
8 |
ኢብራሂም መሀሐመድ ኑር |
ዮርዳኖስ ንጉሴ |
መኖሪያ ቤት |
188 ካ.ሜ |
0264/08 |
ኦሮሚያ ብ/ክ/መ ኦለንጭቲ ከተማ |
2,973,853.00 |
በድጋሚ |
“ |
|
9 |
አል-ባብ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ |
ፈትያ ነጃ |
የንግድ ቤት |
400 ካ.ሜ |
737990/98 |
ኦሮሚያ ብ/ክ/መ አዳማ ከተማ |
15,063,471.94 |
በድጋሚ |
“ |
|
10 |
ሲሳይ ሞሴ |
ላመነው ከበደ |
መኖሪያ ቤት |
200 ካ.ሜ |
Sul/413/05 |
ሸገር ከተማ ሱሉልታ መነ አብቹ ክ/ከ አትሌት ሰፈር |
8,875,095.52 |
በድጋሚ |
“ |
|
11 |
ጂዲ ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ |
መሐመድ ኑር አሊ |
መጋዘን |
1736 ካሜ |
1081/93 |
ኦሮሚያ ብ/ክ/መ አዳማ ከተማ ቀበሌ 01 |
25,856,220.81 |
በድጋሚ |
“ |
|
12 |
ኑረበላይ ኃ/የተ.የግ/ማ |
ኤፍሬም ኃይሌ |
የፋብሪካ መጋዘኖች |
20000 ካ.ሜ |
ደብኢፓ/0325/2011 |
አማራ ብ/ክ/መ ደብረብርሃን ከተማ ቀ07 |
136,783,109.90 |
በድጋሚ |
“ |
|
13 |
አቤል ቃለአብ |
ሰብለወርቅ ግርማ |
ጅምር ሕንጻ |
325.31 ካ.ሜ |
ETH000010254763 |
አደማ ከተማ ጎሮ ቀበሌ |
10,045,022.39 |
በድጋሚ |
“ |
|
14 |
ማርቁማ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማ |
መሰረት ክበበው |
G+3 መኖሪያ ቤት(ግንባታው ያልተጠናቀቀ) |
245 ካ.ሜ |
LMK1031918 46245482118 |
አዲሰ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ ወረዳ 02 |
24,040,790.28 |
ለመጀመሪያ ጊዜ |
“ |
|
15 |
ብሩክ አበበ |
ትዕግስት አለማየሁ |
የፋብሪካ መጋዘኖች |
2499.75 ካ.ሜ |
ET000010253764 |
አዳማ ከተማ ደጋጋ (05) ቀበሌ |
46,403,850.51 |
ለመጀመሪያ ጊዜ |
“ |
|
16 |
ጌታሁን መለሰ |
አዜብ ታደሰ |
G+1 መኖሪያ ቤት |
341 ካ.ሜ |
BOLE/10/9/9/4/2 4248/109111/02 |
አዲስ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ ወረዳ 10 |
34,724,434.52 |
ለመጀመሪያ ጊዜ |
“ |
Tender details
- Deadline: 2026-06-16
- Bid closing time: 10:30
- Bid opening: 2026-06-16 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Bank of Abyssinia S.C.
- Buyer address: Addis Ababa Ethiopia
- Bid bond: 25%
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published: May 17, 2026
- Posted at: 2026-05-18T12:35:27.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.