የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተለያዩ ንብረቶችን ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ
አዲስና በድጋሚ የወጣ የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶች ጨረታ ቁጥር 012/2025/26

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተለያዩ ንብረቶችን ማለትም የተለያዩ ያገለገሉ ፈርኒቸሮች፣ የተለያዩ ያገለገለ የተሽከርካሪ ጎማዎች የቪ8 ተሸከርካሪ ዕቃ መጫኛና የአልሙኒየም ጀርካኖች፣ የተቃጠለ የሞተር ዘይት ከነበርሜሉ፣ ንታይ ቴለር ካውንተሮች የእንጨት ፓሌቶች እና የተለያዩ ያገለገሉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

1. ስለ አሻሻጡ የተዘጋጀውን ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን ሰነደ ቄራ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 211 የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ከግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ግንቦት 26 ቀን 2018 ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ባሉት የስራ ቀናት መግዛት ይችላሉ።

2. ተጫራች ያገለገሉ ንብረቶችን ከግንቦት 13 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ያገለገሉ ንብረቶችን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቃሊቲ ቅርንጫፍ ትይዩ ባለው አስፓልት ወደ ውስጥ ገባ ብሎ በሚገኘው የቀድሞ ብራሌ ጥጥ መዳመጫ ግቢ ውስጥ እንዲሁም የተቃጠለ የሞተር ዘይት የሚገኝበት ቦታ ቃሊቲ ከመንገድ ትራንስፖርት የማሽከርከር ብቃት ማረጋገጫ እና ማሰልጠኛ ተቋም አጠገብ በሚገኘው የባንኩ ተሽከርካሪዎች ጥገና ጋራዥ /የቀድሞው አማልጋ ሜትድ/ ግቢ ውስጥ ከጠዋቱ ከ2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ባሉት የስራ ቀናት በመገኘት ማየት ይችላል።

3. የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ላይ ታዛቢዎች በተገኙበት ይታሸጋል።

4. ተጫራች ለንብረቱ የሚሰጠውን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ባለው ክፍት ቦታ በመሙላት የጨረታ ማስከበሪያ እና ሌሎችም አስፈላጊ ሰነዶችን በፖስታ በማሸግ ቄራ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሕንፃ 2ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት እስከ 4፡00 ሰዓት ብቻ ያስገባል።

5. የተቃጠለ የሞተር ዘይትና ያገለገሉ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች የማስወገድ ወይም መልሶ ለመጠቀም ከኢፌድሪ የአካባቢ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ፈቃድ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።

6. ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ታዛቢዎች በተገኙበት ቄራ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 2ኛ ፎቅ በግልጽ ይከፈታል።

7. ተጫራች ለሚጫረትበት የንብረት ዓይነቶች የጨረታ የመነሻ ዋጋውን 25% (ሃያ አምስት በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለያገለገሉ ንብረቶች አስወጋጅ (Commercial Bank of Ethiopia Disposal) በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

8. ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ሲፒኦ አሸናፊ ለሚሆነው በሚገዛው ንብረት ክፍያ ላይ የሚታሰብ ሲሆን አሸናፊ ላልሆኑት ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።


Tender details

  • Deadline: 2026-06-05
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-06-05 10:15
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Commercial Bank of Ethiopia
  • Bid bond: 25%
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: May 17, 2026
  • Posted at: 2026-05-18T12:59:43.000Z
  • Buyer website: https://www.combanketh.com

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders