የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት እጅጋየሁ አላዩ እና በፍ ባለዕዳ እነ መሰረት አላዩ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 199981 23/10/2017 ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ እና በኮ/መ/ቁ/205637 በ29/03/2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 09 የቤት ቁጥር 514 የሆነው በሟች አቶ አላዩ ወንዝነህ ስም የሆነው ሰነድ አልባ የሆነ ቤት በይዞታ ውስጥ 1ኛ ተከሳሽ የሰሩት 87.21 ካ/ሜ ላይ ያረፈ 4 ክፍል ሳሎን ሁለት መኝታ እና ምግብ ቤት ያረፈበት ቤት ሳይጨምር የቤቱ ስፋት 70.37ካ/ሜ ከአጠቃላይ ይዞታው ላይ ፍርድ ያላረፈበት እና የማይሸጥ 87.21 ካ/ሜ ሲቀነስ ቀሪው ይዞታ 363.79 ካ/ሜ ካርታ የሌለው ሰነድ አልባ በወንዝ ልማት ዳርቻ የተያዘ ሆኖ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 10,904,800.45 (አስር ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ አራት ሺህ ስምንት መቶ ከ45/100) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሰኔ 11ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው 5፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-18
- Bid closing time: 11:30
- Bid opening: 2026-06-18 11:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published: May 18, 2026
- Posted at: 2026-05-19T06:45:51.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.