በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ያገለገሉ የፈርኒቸር ዕቃዎች፣ የተሰባበሩ የብረት አልጋና ፍራሽ፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና የህክምና ማሽኖች፣ ሌሎች ያገለገሉ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

ያገለገሉ ዕቃዎች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ መለያ ቁጥር መ.ኢ.ኮ 001/2018

በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ያገለገሉ ዕቃዎች ማለትም የተለያዩ፣- ፈርኒቸር ዕቃዎች፣ የተሰባበሩ የብረት አልጋና ፍራሽ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና የህክምና ማሽኖች ሌሎች በሰነዱ ላይ የተጠቀሱትን ያገለገሉ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

 በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ገዢዎች በጨረታ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

  • ተጫራቾች ለ2018 ዓ.ም የሚያገለግል ከመስኩ ጋር አግባብነት ያለው ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ሆነው የማስረጃውን ኮፒ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፣
  • ለተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ እየከፈለ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሙሉ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት በኮሌጁ ፋይናንስ ዴስክ በቢሮ ውስጥ መውሰድ የሚችሉ መሆናችሁን እየገለፅን የተዘጋጁትን ዕቃዎች በስራ ሰዓት በዋናው ግምጃ ቤት በመገኘት መመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
  • ተጫራቾች ኮሌጅ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በጥንቃቄ በመሙላት የድርጅታቸውን ህጋዊ ማህተም እና ፊርማ በማስቀመጥ መሙላት ይኖርባቸዋል።
  • ማንኛውም ተጫራች በሌሎች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም።
  • ተጫራቾች ዋጋ የሞለበትን የጨረታ ሰነድ በታሸገ ፖስታ ኤንቨሎፕ አድርገው እስከ ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ድረስ ብቻ በግዥ ዴስክ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ያለባቸው መሆኑን። ጨረታው ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ተዘግቶ በዕለቱ 4፡45 ተጨራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጁ አዳራሽ ይከፈታል።
  • ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ብቻ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
  • መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- በስልክ ቁጥር፡- 09 12 15 66 30 መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ


Tender details

  • Deadline: 2026-05-24
  • Bid closing time: 10:30
  • Bid opening: 2026-05-24 10:45
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ
  • Bid bond: 10,000.00 (አስር ሺህ ብር)
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: May 18, 2026
  • Posted at: 2026-05-19T07:16:01.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders