የቦታው ስፋት 368 ካ/ሜ የሆነ ቤትና ቦታ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፍ/ባለመብት አቶ ሽብሩ ማሞ እና በፍ/ባለዕዳ እነ ወ/ሮ ተስፋነሽ ፍስሀ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 137699 በጥቅምት 13 ቀን 2016 ዓ/ም እና በ18/03/2016 ዓ/ም በኮ/መ/ቁ/00675 በ20/5/2016 ዓ/ም በ24/8/2016 ዓ/ም በ26/11/2016 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 5 የቤት ቁጥር 199 የሆነውን በይዞታ መለያ ኮድAA000060502548 በሆነ የተመዘገበውን የቦታው ስፋት 368 ካ/ሜ የሆነ ቤትና ቦታ ፍርድ ያረፈበት ቤት ካርታ ያለው የወለል ስፋት 273.01 ቤቱ መኖሪያ ስለሆነ ካፒታል ጌን ታክስ አይከፈልም በባለሙያ ግምት የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 30,774,092 (ሰላሳ ሚሊዮን ሰባት መቶ ሰባ አራት ሺህ ዘጠና ሁለት ብር) ሆኖ በሐራጅ ይሸጣል የሚል ማስታወቂያ ወጥቶ በእለቱ ተጫራች አልቀረበም። ይህንኑ ለፍ/ቤቱ ሪፖርት ተደርጎ ፍ/ቤቱ በ14/11/17 ዓ/ም በድጋሚ ጨረታ እንዲወጣ ትዕዛዝ የሰጠ በመሆኑ በሁለተኛ ጨረታ የግምቱን 1/4ኛ ብር 7,686,023 (ሰባት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሰማኒያ ስድስት ሺህ ሀያ ሦስት ብር) በማስያዝ መሳተፍ የሚቻል ሆኖ የስም ማዛወሪያ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 4፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት/ ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ አፈ/ዳይሬክቶሬት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-18
  • Bid closing time: 10:30
  • Bid opening: 2026-06-18 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
  • Bid bond: 25%
  • Published: May 18, 2026
  • Posted at: 2026-05-19T07:26:27.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders