የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት የቢሮ መገልገያ መሳሪያዎች (ፎቶኮፒ ማሽን፣ ፕሪንተር፣ ዓርማ የሚታተምባቸው ቲሸርቶች፣ እስክሪብቶ፣ አጀንዳ፣ ቢልቦርድ እና ሌሎችም) ግዥ መፈፀም ይፈልጋል

Description

የቢሮ መገልገያ መሳሪያዎች (ፎቶኮፒ ማሽን፣ ፕሪንተር፣ ዓርማ የሚታተምባቸው ቲሸርቶች፣ እስክሪብቶ፣ አጀንዳ፣ ቢልቦርድ እና ሌሎችም) ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ቁጥር፦ ስተአ/004/2026

የአገልግሎት መ/ቤታችን እ.ኤ.አ በ2026 በጀት ዓመት ለስራ አገልግሎት የሚውል የቢሮ መገልገያ መሳሪያዎች (ፎቶኮፒ ማሽን፣ ፕሪንተር፣ ዓርማ የሚታተምባቸው ቲሸርቶች፣ እስክሪብቶ፣ አጀንዳ ፣ ቢልቦርድ እና ሌሎችም) ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የሚፈለግባቸውን ማንኛውንም የመንግሥት ግብር አጠናቅቀው ለመክፈላቸው ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ፣ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ በጨረታ ለመሳተፍ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ መንግስት ግዥ እና ንብረት ባለስልጣን በአቅራቢነት የተመዘገቡ እንዲሁም የተ.እ.ታ. ምዝገባ ሠርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን፣ በብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ዘዴ አወዳድሮ ውል በመግባት የሚፈፀም ይሆናል።

በመሆኑም ተጫራቾች፡-

1) የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 እንቁላል ፋብሪካ ወይምየፌዴራል ፖሊስ ክብብ ፊት ለፊት ከሚገኘው የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ዋና መ/ቤት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የፋይናንስ ቡድን ቢሮ በመምጣትና የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል ለ10 ተከታታይ ስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት እስከ 6፡30 ሰዓት ፣ ከሰዓት ከ7፡30 እስከ 11፡30 ባለው ጊዜ ውስጥ መግዛት ይቻላሉ። ቅዳሜና እሁድ የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ስራ ቀናት አይደሉም።

2) ማንኛውም ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ጥቅል ዋጋ 2/ሁለት/ በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በFD.R.ERefugees and Returnees Service ስም በተዘጋጀ የባንክ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በቅድመ-ሁኔታ ያልተገደበ የባንክ ዋስትና ደብዳቤ፣ የአገልግሎቱን ዋጋ፣ በቀረበው ዝርዝር የፍላጎት መግለጫ መሰረት የቴክኒክ ሰነድ እና እንዲሁም በጨረታ ሰነዱ የተዘረዘሩትን የብቃትና የልምድ ማስረጃዎች ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የሚያያዙ ማስረጃዎች በሙሉ የአገልግሎት ጊዜያቸው ያላበቃላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።

3) የመጫረቻ ሰነዳቸውን ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ሰነድ አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ለየብቻው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር እስከ 10ኛው የስራ ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ ከታች በተመለከተው አድራሻ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአገልግሎት መስሪያ ቤቱ የሰራተኞች ክበብ ምድር ቤት ይከፈታል። ሆኖም ይህ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓላት ቀን ከዋለ፣ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት ይሆናል።

4) መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ
የእንቁላል ፋብሪካ አደባባይን ሳይሻገሩ
ከፌዴራል ፖሊስ ክበብ ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር 09-97-23-66-31
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-28
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10ኛው የስራ ቀን 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-05-28 14:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10ኛው የስራ ቀን 8፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Refugee and Returnee Service
  • Buyer address: ከዋሽንግተን የህክምና ማዕከል 500 ሜትር ያህል ገባ ብሎ ወደ ቦሌ ሚካኤል በሚወስደው መንገድ ላይ
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 200.00 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published: May 18, 2026
  • Posted at: 2026-05-19T08:35:43.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders