በሸገር ከተማ አስተዳደር የገፈርሳ ጉጄ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት የገፈርሳ ጉጄ ክፍለ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ቄራ ለማከራየት ይፈልጋል

Description

የቄራ ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ

በሸገር ከተማ አስተዳደር የገፈርሳ ጉጄ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት የገፈርሳ ጉጄ ክፍለ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ቄራ ለማከራየት ይፈልጋል።

በዚሁ መሬት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች የሚያሟሉ ተጫራቾች ዝርዝር የጫረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የገፈርሳ ጉጄ ከፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ ቤት በሲንቄ ባንክ በተከፈተው ሒሳብ ቁጥር 1065173571213 የማይመለስ ብር 2000.00 (ሁለት ሺህ ብር ግቢ በማድረግ የገቢ ደረሰኝ የገፈርሳ ጉጄ ክፍለ ከተማ ከተማ መግዛት ይችላሉ።

1. ተጫራቾች በሚያቀርቡት በዘርፉ ሕጋዊ የተደሰ ንግድ ፈቃድ በስማቸው ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን፣ እንዲሁም በፌዴራል ገ/ ሚኒስቴር ወይም በኦሮሚያ ዝቢሮ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የቫት (የተጨማሪ እሴት ታክስ) ተመዝጋቢና የመዝገባ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችልና በዘርፉ ከክልሉ የእንስሳት ጤና ኤጀንስ የድጋፊ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የዕቃ ዓይነት የጨረታ ማስከበሪያ 100,000.00 (መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት (CPO) ከጨረታው ሠነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

3. (አንድ) ቫን የሥጋ መኪናዎች ማቅረብ የሚችልና ወይም ከዚያ በላይ ያለው እና በሥጋ አቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4. የጨረታው ሰነድ በግልጽ ኦሪጅናልና ኮፒ ለየብቻ ታሽጎ በፖስታው ላይ ተጽፎ ለየብቻው ታሽጎ የተከራዩ ስም ተጽፎበት ማቅረብ ይኖርበታል።

5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በመሙላት በኦርጅናል እና በኮፒ በመለየት አሽጎ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ የሥራ ቀን እስከ 16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት አድራሻ ገ/ጉጄ ከፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢቂልቱ ሕንፃ አራተኛ ፎቅ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

6. ጨረታው በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በገፈርሳ ጉጄ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት አራተኛ ፎቅ ውስጥ ይከፈታል። 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።

7. የጨረታው አሸናፊ ለመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና 1ዐ% Performance Boad በማስያዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል።

ማሳሰቢያ፡-

ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ከመደበኛ የሥራ ቀናት ውጭ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል። አሠሪው መ/ቤት የተሻለ መንገድ ከአገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተጨማሪ ማብራሪያ ከተፈለገ በስልክ ቁጥር (09 49 53 95 45) ወይም(09 52 81 85 58) ደውለው መረዳት ይችላሉ።

ገፈርሳ ጉጂ

በሸገር ከተማ አስተዳደር የገፈርሳ ጉጄ ክፍለ ክተማ

ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-04
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ የሥራ ቀን እስከ 16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት
  • Bid opening: 2026-06-04 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ የሥራ ቀን እስከ 16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሠዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Sheger City Administration Gefersa Guje Sub-city Finance Office
  • Bid bond: 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/
  • Bid document price: 2000.00 ብር
  • Published: May 18, 2026
  • Posted at: 2026-05-19T09:19:07.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders