የመኖሪያ ቤት ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ

Description

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በአፈጻጸም ከሳሾች

1. አለምነሽ ካሳ

2. ህጻን ዳንኤል መኮነን እና

በአፈጻጸም ተከሳሾች ፡

1. ማቲያስ መኮነን

2. እዩኤል መኮነን

3. ሩት መኮነን

4. ዮሀንስ አሊ መካከል ስላለው የአፈጻጸም ክስ ከርከር ጉዳይ

የአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት ደሴ ምድብ ችሎት ግንቦት 04 ቀን 2018 በዋለው ችሎት በሰጠው ትእዛዝ መሰረት ለአፈጻጸም መነሻ የሆነው ቤትና ቦታ በደሴ ከተማ ሆጤ ክፍለ ከተማ ባህል አምባ ቀበሌ ልዩ ቦታው ደሴ ሪፈራል ሆስፒታል ዝቅ ብሎ ቦርከና ወንዝ አካባቢ የሚገኝ በሰሜን ጥራጥሬ ድርጅት፣ በደቡብ መንገድ፣ በምስራቅ ወንዝ እንዲሁም በምዕራብ ይመር ሠይድ አዋሳኝ ያለ መኖሪያ ቤት እና ተቀጥሎ የተሠራ የዶሮ ቤት ጠቅላላ መነሻ ዋጋ ብር 3,650,640 (ሶስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሀምሳ ሺ ስድስት መቶ አርባ ብር እንዲሸጥ ትዕዛዝ የተሠጠ ስለሆነ ማንኛውም መጫረት የሚፈልግ አካል ሰኔ 13 ቀን 2018 ከቀኑ 7፡00 ሰአት ላይ በመገኘት የግልጽ ጨረታው ተሳታፊ መሆን የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

ማሳሳቢያ

  • ጨረታው ከቀኑ 7፡00 ሠዓት ላይ ጀምሮ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ ይጠናቀቃል።
  • የተጫራቶች የምዝገባ ሠዓት ከቀኑ 7፡00 ሠዓት እስከ 9፡30 ሰዓት ድረስ ብቻ መሆኑን እንገልጻለን።
  • በጨረታው የሚሳተፍ ማንኛውም አካል ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ ይዞ መገኘት አለበት።
  • ጨረታውን የሚያሸንፍ አካል ያሸነፈበትን ብር መጠን 1/4ኛ ወዲያውኑ ለሀራጅ ባዩ ባለሙያ ማስያዝ አለበት።
  • ጨረታውን የሚያሸንፍ አካል በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ማድረግ አለበት።
  • ጨረታው የሚካሄደው ከላይ በተገለጸው አድራሻ መሠረት ቤቱ በሚገኝበት ቦታ መሆኑን እንገልጻለን።

የአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት ደሴ ምድብ ችሎት

 


Tender details

  • Deadline: 2026-06-20
  • Bid closing time: 13:00
  • Bid opening: 2026-06-20 13:00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: ANSR Supreme Court Dessie Divisional Court
  • Published: May 19, 2026
  • Posted at: 2026-05-19T11:59:36.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders