የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለሙበት ዝናቤ ሲሳይ እና በፍ/ባለዕዳ እነ አቶ ነጋሽ ሄይ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.184668 በ03/10/2016ዓ.ም እና የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.209946 በቀን 30/7/2018ዓ.ም በዋለው ችሎት በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ውስጥ የሚገኝ የቤት ቁጥር 9999/1/አዲስ/ በቁጥር YK117184459208272 የተመዘገበ ካርታ ያለው የይዞታ ስፋት 208 ካ/ሜ በልኬት የተገኘው የቦታ ስፋት 236 ካ/ሜ ሲሆንይህን በልኬት የተገኘ ስፋት በስተምስራቅ በኩል በከፊል ከአጎራባች ጋር ያለው ድንበር በወሰናቸው መሰረት የታጠረ ባለመሆኑ በልኬት የተገኘው የቦታ ስፋት ሊቀነስ ወይም ሊጨመር የሚችል ሆኖ ከአጠቃላይ ይዞታ በካርታ ከተያዘው ላይ 6ኛ ዙር የመንገድ ጥናት 9.56 ካ/ሜ ይነካዋል በካርታ መሰረት በሐራጅ የሚሸጠው በብሎኬት የተሰራ 3 ክፍል ሰርቪስ ቤቶች ወይም የ6ኛ ተስማሚ የአቶ ተመስገን ፋንታሁን ሲሳይ ቤት የተባለውን ሳይጨምር የሐራጅ መነሻ 5,902,340 ( አምስት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሁለት ሺህ ሶስት መቶ አርባ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ4፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4ኛውን በኢትጵዮያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ C.P.O የሚያመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ ቤት ስም CPO በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-22
- Bid closing time: 10:30
- Bid opening: 2026-06-22 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት
- Bid bond: 25%
- Published: May 19, 2026
- Posted at: 2026-05-19T12:28:40.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.