Vehicle and Machinery Sale

የደቡብ ምኢ /ኢት/ሕ/ክ/መ/ፋይናንስ ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ያገለገሉ/አገልግሎት/ የማይሰጡ ተሽከሪካሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የደቡብ ምኢ /ኢት/ሕ/ክ/መ/ፋይናንስ ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ያገለገሉ/ አገልግሎት/ የማይሰጡ ተሸከሪካሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በዚሁ መሠረት ጨረታው በማንኛውም የሥራ መስክ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦችን ድርጅቶችን የሚጋብዝ ሲሆን በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች አሟልተው መገኘት አለባቸው።

1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ግዥ የማይመለሰ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ በግዥ ፋይ/ ሰም በተከፈተው አካውንት ቁጥር 1000454348471 ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዱን ከጋራ ግዥና ንብረት ማስወገድ ዘርፍ መውሰድ ይችላሉ።

2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በእያንዳንዱ ተሽከርካሪ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ/ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ፋይናንሰ ቢሮ ስም በማሠራት ከጨረታ ሰነድ ጋር በማዘጋጀት አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3 ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ተሸከርካሪ ኮድና ሰሌዳ ቁጥር ልክ /መስመር/ ላይ ባለው የዋጋ መሙያ ቦታ ላይ የሚገዙበትን ዋጋ በመሙላት ኦሪጅናልና ኮፒውን በመለየት በታሸገ ኤንቨሎፕ በማዘጋጀት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ይፋ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ድረስ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውሰጥ ማስገባት ይችላሉ።

4. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ በ4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ሆኖም የተጫራቾች ወይም ተወካዮች ያለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያስተጓጉልም። 16ኛው ቀን የመንግሥት የሥራ ቀን ሆኖ ካልተገኘ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።

5. ተሸከሪካሪዎችን ማየት ወይም መጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች በዋጋ ማቅረቢያ ላይ በተዘረዘሩት ቦታዎች ላይ በመገኘት ይህ ማስታወቂያ ይፋ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ እስከ አስራ አምስተኛው ቀን ድረስ ባሉት የመንግሥት የሥራ ቀንና ሰዓት ማየት ማረጋገጥ| ይችላሉ።

6. አሸናፊ ተጫራች ያሸነፋቸውን ተሸከርካሪዎች ሙሉ ክፍያ ፈጽመው በ20 ቀናት ውስጥ ማንሳት የሚጠበቅባቸው ሲሆን ክፍያው እንደተፈጸመ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ይመለሰላቸዋል።

7. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር-047 331 1888 ደውለው ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግሥት

ፋይናንስ ቢሮ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-03
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ይፋ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-03 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ይፋ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: South West Ethiopia Region
  • Publishing entity: ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ
  • Bid bond: በእያንዳንዱ ተሽከርካሪ 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (May 19, 2026)
  • Posted at: 2026-05-19T12:43:32.000Z
← Back to all tenders