የደሴ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ ለተለያዩ አገልግሎት የሚውል የግንባታ ብረታ ብረቶች እና ሌሎች ብረታ ብረቶችን በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
የደሴ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ ታክስ ከፋዩ አቶ እስማኤል አህመድ ሁሴን የሚፈለግባቸውን ግብር ታክስ ብር 119,809,879.00 (አንድ መቶ አስራ ዘጠኝ ሚሊዮን ስምንት መቶ ዘጠኝ ሺህ ስምንት መቶ ሰባ ዘጠኝ ብር) ስላልከፈሉ አድራሻው አማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ደሴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ የሚገኘውን የታክስ ባለዕዳውን ንብረት የሆኑትን ለተለያዩ አገልግሎት የሚውል የግንባታ ብረታ ብረቶች እና ሌሎች ብረታ ብረቶችን የገቢዎች ቢሮ በአዋጅ ቁጥር 241/2008 አንቀጽ 41 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር እንድትችሉ ይጋብዛል።
1. የሀብቱ የጨረታ መነሻ ዋጋ ግምት
2. ስለሀብቱ አሻሻጥ መረጃ ከደሴ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ የገቢ አወ/አሰ/ክት/ ቡድን ክፍል ማግኘት ይቻላል።
3. ስለሃብቱ አጠቃላይ መረጃ እና ያለበትን ሁኔታ ደሴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ ዘወትር በስራ ሠዓት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት በአካል በመገኘት ማየት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን የእቃዎች ዝርዝር፣ አይነት እና ብዛት የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሠዓት ደሴ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ ቢሮ ቁጥር 12 የማይመለስ ብር 500.00(አምስት መቶ ብር) በመክፈል ማግኘት ይችላሉ።
5. ተጫራቾች በቅድሚያ የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/10ኛውን ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ አለባቸው።
6. ተጫራቾች ሀብቱን የሚገዙበትን ዋጋ በግልጽ በማስፈር በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ አድርገው አድራሻው ደሴ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ በማለት አስፍረው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 12 በተዘጋጀው የግልጽ ጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
7. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ደሴ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ ይከፈታል።
8. ከላይ በተራ ቁጥር የተጠቀሰው ቢኖርም የጨረታ መክፈቻው ቀን በእለቱ ከስራ ቀን ውጪ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሠዓትና ቦታ ይከፈታል።
9. አሸናፊው ተጫራች የሚለየው በእያንዳንዱ ሎት በተጠየቁት ጠቅላላ ዝርዝሮች በሙሉ በድምሩ (lot) ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበው ይሆናል። በዚህ መስፈርት መሠረት ለሁሉም ዝርዝር ዋጋ ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታ ውድድር ውጭ ይሆናል።
10. አሸናፊው ያስያዘው ገንዘብ ከገዥው ዋጋ ጋር ታስቦ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ አጠናቆ በመክፈልና ሀብቱን መረከብ አለበት።
11. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 ቀናት ውስጥ አጠናቆ የማይከፍል ከሆን ለጨረታው በዋስትና ያስያዘው ገንዘብ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ የጨረታው አሸናፊነቱ ይሠረዛል።
12. ገቢዎች መምሪያው ስለሀብቶቹ አሻሻጥ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል ሊሠረዝ ይችላል።
የደሴ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-06-03
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-06-03 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: በደሴ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት
- Bid bond: 10%
- Bid document price: 500.00(አምስት መቶ ብር)
- Published: May 19, 2026
- Posted at: 2026-05-19T13:03:55.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.