የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ሰሜን ምዕራብ ሪጅን ደባርቅ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ቤት መከራየት ይፈልጋል

Description

የቢሮ ኪራይ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ሰሜን ምዕራብ ሪጅን ደባርቅ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ቤት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከመስከረም 16/2019 ዓ/ም ጀምሮ ለ5 አመት መከራየት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም፡-

1. በስማቸው የይዞታ ማረጋገጫ ያላቸው

2. የዘመኑ የአፈር ግብር የከፈሉበት ማሰረጃ ያላቸው

3. ለቢሮ አገልግሎት የሚፈለገው ቤት ለአገልግሎት ምቹ እንዲሆን ህንፃው ግራውንድ /G+0/ ያለው ሆኖ ከ2ተኛ ፎቅ ያልበለጠ፣ ወለሉ ሴራሚክ የሆነና ከ12 ከፍሎች በላይ ያሉትና

  • የ3 ክፍሎች ስፋት እያንዳንዳቸው 40 ካሬ ያላነሱ
  • የ5ቱ ክፍሎች ስፋት እያንዳንዳቸው ከ20 ካሬ ያላነሱ እንዲሁም
  • የ4ቱ ክፍሎች ስፋት እያንዳንዳቸው ከ15ካሬ ያላነሱ መሆን አለባቸው፡፡

4. ለተገልጋይ ምቹ የሆነና ከመሃል ከተማ ያልራቀና ከዋናው አስፓልት መንገድ ወደ ውስጥ 600 ሜትር መብለጥ የለበትም እንዲሁም በአካባቢው የተዘረጋ የስልክ መስመር ያለው

5. የቧንቧ ውሃ፣መብራት የራሱ ቆጣሪና የተሟላ ሶኬት ያለው፣ንፁህ መፀዳጃ ቤትያለው

6. የጥበቃ ቤት ያለው ከሌለው ለመስራት ፈቃደኛ የሆነ

7. የራሱ ግቢና አጥር ያለው

8. የቤቱ ስፋት ከ21 ሰራተኞች በላይ ሊይዝ የሚችል፡፡

ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-8 የተጠቀሱትን የሚያሟሉ ተጨራቾች የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ደባርቅ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ድረስ በመቅረብ የመጫረቻ ሰነዱን ዋጋ 100.00 ብር ከፍለው በመወሰድና የሚከራዩትበትን ዋጋ በመሙላት ከይዞታ ማረጋገጫ እና የአፈር ግብር የተከፈለበት ማሰረጃ ጋር በደንብ በታሸገ ፖስታ በጽ ቤታችን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ የምንከራየው ቤት ለተገልጋይ አመች መሆኑ በኮሚቴ የሚረጋገጥ ይሆናል፡፡ ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ 8፡30 ሰዓት በጽ/ቤቱ ተጨራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጨራቾች ባይገኙም ከመክፈት አያግደውም፡፡ የህዝብ በዓላት ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡

ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ
አድራሻ፡-ደባርቅ ከተማ ጃይንት ሆቴል ካለው ህንጻ አማራ ባንክ ጀርባ
ለተጨማሪ መረጃ ፡-በስልክ ቁጥር-058 417 0093/058 417 9803/
የመንግሥት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ሰሜን ምዕራብ ሪጅን ደባርቅ ቅ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-30
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-05-30 14:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Public Servants' Social Security Administration
  • Buyer address: Addis Ababa, Ethiopia
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published: May 20, 2026
  • Posted at: 2026-05-20T08:16:10.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders