የቤት የሐራጅ ሸያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሸያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለሙበት እነ ሙሉጌታ የማነህ እና በፍ/ባለዕዳ ብሩክታዊት ግርማይ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.204899 በየካቲት 18 ቀን 2018 ዓ.ም እና የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.20774 በቀን 25/9/2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 01 ውስጥ የሚገኝ የቤት ቁጥር 10 በመለያ ቁጥር AA 0000801044761310110 የሆነ የቦታ ስፋት 36.74 ካ/ሜ ካርታ ያለው የሐራጅ መነሻ 1,469,777.08 (አንድ ሚሊዮን አራት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ሺህ ሰባት መቶ ሰባ ሰባት ከ08/100) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በኢትጵዮያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.PO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤጽ/ስም C.RO አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዞወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-23
- Bid closing time: 11:00
- Bid opening: 2026-06-23 11:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት
- Bid bond: 25%
- Published: May 20, 2026
- Posted at: 2026-05-20T08:26:32.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.