የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለበረራ መስተንግዶ (Inflight Catering)፣ ለስካይላይት ሆቴል እና ለሠራተኞች ካፍቴሪያ አገልግሎት የሚውል ነጭ የስንዴ ዱቄት (white wheat flour) ምርት ከሚያመርቱ ድርጅቶች ጋር በኮንትራት ስምምነት ለሶሥት (3) አመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመስራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር:- SSNT-T617
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለበረራ መስተንግዶ (Inflight Catering)፣ ለስካይላይት ሆቴል እና ለሠራተኞች ካፍቴሪያ አገልግሎት የሚውል ነጭ የስንዴ ዱቄት (white wheat flour) ምርት ከሚያመርቱ ድርጅቶች ጋር በኮንትራት ስምምነት ለሶሥት (3) አመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመስራት ይፈልጋል።
ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡-
በአገልግሎቱ ዘርፍ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፤ ለ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ሥራ ፊቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ(TIN) ምዝገባ ወረቀት ያለው፣የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ ፣ አንድ (1) ዓመትና ከዛ በላይ የሰራ ተጫራች በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናትበአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ አንድ መቶ ብር (ብር 100.00) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T617 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ቅጂውን (scan copy) በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ።
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሃምሳ ሺህ ብር (50,000.00) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው። ከማንኛውም ኢንሹራንስ ተቛም እና ቅድመ ሁኔታ ያለው የባንክ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም።
ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጨረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9:00 ሰዓት ይከፈታል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ:
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ዋና መስሪያ ቤት
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል
ስልክ ቁጥር፡ 011-517-4552
ወ/ሮ ብርቱኳን ሰሙ
ኢ-ሜይል: birtukans@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
Tender details
- Deadline: 2026-06-22
- Bid closing time: 14:30
- Bid opening: 2026-06-22 15:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Airlines
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
- Published: May 20, 2026
- Posted at: 2026-05-20T08:29:04.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.