Grains, pulses and staples
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢሾፍቱ ከተማ የሚገኘው የእንስሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ ለ2019 በጀት ዓመት የተማሪዎች ምግብ ቤት የሚውል የተለያዩ የምግብ ጥሬ ዕቃዎች መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር እ/ህ/ግ/ኮ 001/2019
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢሾፍቱ ከተማ የሚገኘው የእንስሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ ለ2019 በጀት ዓመት የተማሪዎች ምግብ ቤት የሚውል የተለያዩ የምግብ ጥሬ ዕቃዎች የወጣ ግልፅ ጨረታ ነው።
ስለሆነም፦
1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና ህጋዊ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸው እንዲሁም በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ የታክስ ከፋይ (Tin No) የምስክር ወረቀት ፣ የአቅራቢዎች ምዝገባ/supplier list እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 213,150.00 / ሁለት መቶ አስራ ሶስት ሺህ አንድ መቶ ሀምሳ ብር/ በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) የባንክ ዋስትና ደብዳቤ/ ቼክ ወይም ጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘው የእንሰሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ ግዥ ክፍል በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን የያዘውን ሰነድ አንድ ቴክኒካል ኦሪጂናልና አንድ ቴክኒካል ኮፒ እና አንድ ፋይናንሽያል ኦርጅናልና አንድ ፋይናንሽያል ኮፒ በእናት ፖስታ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት እስከ 16ኛው ቀን 7፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በኮሌጁ ግዥ ክፍል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን በ7፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ8፡00 ሰዓት በግልፅ ይከፈታል። የመክፈቻ ቀኑ የህዝብ በዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው መዝጊያ ሰዓት ታሽጎ በግልጽ ይከፈታል።
7. በጨረታ መክፈቻ ቀኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አይስተጓጎልም።
8. ተጫራቾች የአሸነፏቸውን አቅርቦቶች በሚሰጣቸው ትዕዛዝ መሰረት በቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘው የእንሰሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ በራሳቸው ትራንስፖርት በማጓጓዝ ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
9. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የእንሰሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ
ስልክ ቁጥር፡- 0114338557/0912065392
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢሾፍቱ ከተማ የሚገኘው
የእንስሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ
Tender details
- Deadline: 2026-08-15
- Bid closing time: 13:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ7፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-15 14:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእንሰሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ
- Bid bond: 213,150.00 /ሁለት መቶ አስራ ሶስት ሺህ አንድ መቶ ሀምሳ ብር/
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Jul 31, 2026)
- Posted at: 2026-07-31T07:44:42.000Z