Grains, pulses and staples

በደቡብ ወሎ ዞን አልብኮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የስንዴ እህል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኩንታል መሸጥ ይፈልጋል

Description

በድጋሜ የወጣ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 05/2018

በአ. ብ.ክ.መ. በደቡብ ወሎ ዞን በአልብኮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ን/አስ/ቡድን በ2018 በጀት ዓመት ከህብረተሰቡ ለተረጂነት የተሰበሰበ የስንዴ እህል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኩንታል መሸጥ ይፈልጋል።

ስለዚህ፣

1. መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች /ድርጅት/ በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የእህል የጥራጥሬ የንግድ ስራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል።

2. ተጫራቾች የአንዱን ኩንታል ስንዴ መነሻ ዋጋ ለጨረታ ከተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ማገኘት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋውን በመሙላት ኦሪጂናል መረጃዎን በታሸገ ፖስታ የጨረታ ማስከበሪያውን ዋስትና የጠቅላላ ዋጋውን 5% % በጥሬ ገንዘብ ከባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ማቅረብ የሚችል።

4. የጨረታ ሰነዱን አልብኮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 14 ድረስ በመገኘት የማይመለስ ብር 200/ ሁለት መቶ ብር/ ብቻ መግዛት ይችላሉ።

5. የጨረታ ሰነዱ በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ይህንን ማስታወቂያ የያዘው ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጅምሮ ለተከታታይ 15 ቀን በአየር ላይ በመቆየት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚያው ቀን ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ይከፈታል፤ ይህ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።

6. ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ40 ተከታታይ ቀናት ይሆናል።

7. የጨረታ ሰነዱ የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙም በአልብኮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ይከፈታል።

8. በወጣው የጨረታ ሰነድ ላይ ጥያቄና ማብራሪያ ቅሬታ ካለዎት በህጉና በአዋጁ መሰረት አልብኮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 19/11 በፅሁፍ ማቅረብ ይችላሉ።

9. በጨረታው አሸናፊ ከሆነ አሸናፊ መሆንዎ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ባሉት በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 10% በጥሬ ገንዘብ ከባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማቅረብ ውል መውሰድ ይችላሉ ውል መውሰድ ካልቻሉ ግን ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ዋስትና ተወርሶ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።

10. በውሉ መሰረት ውል የገቡበትን ጠቅላላ ዋጋ በአልብኮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በሚሰጠዎት የባንክ አካውንት ቁጥር ሙሉ በሙሉ በማስገባት የገቢ ደረሰኙን በመያዝ እህልዎን በመረከብ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃለው ማንሳት የሚጠበቅብዎት ሲሆን ነገር ግን በተባለው ጊዜ ሳያነሱ ቀርተው ብልሺት ወይም ጉዳት ቢደርስበት ሻጭ ተጠያቂ ወይም ሀላፊነት ሊወስድ አይችልም።

11. ሻጭ ማንኛውንም ወጭ የማይሸፍን መሆኑን መገንዘብ ይኖርቦታል።

12. መ/ቤቱ የተሸለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ ህጋዊ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 215 0009/32 መደወል ይችላሉ።
በአ.ብ.ክ.መ. በደቡብ ወሎ ዞን አልብኮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-22
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህንን ማስታወቂያ የያዘው ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጅምሮ በ16ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-22 12:00
  • Bid opening (note): ይህንን ማስታወቂያ የያዘው ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጅምሮ በ16ኛው ቀን 5፡00 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Albeko Woreda FEDB
  • Bid bond: 5%
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 07, 2026)
  • Posted at: 2026-08-07T07:13:31.000Z
← Back to all tenders