Grains, pulses and staples

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በዋግ ኸምራ ሰቆጣ ከተማ የዋቢ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ማበራት ዩንዬን ኃ/የተወሰነ ጤፍ መግዛት እንዲሁም የባቄላ ክክ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በዋግ ኸምራ ሰቆጣ ከተማ የዋቢ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ማበራት ዩንዬን ኃ/የተወሰነ 1ኛ ደረጃ ቀይ ጤፍ 600 ኩንታል፤ 1ኛ ደረጃ ሰርገኛ ጤፍ 1400 ኩንታል፣ 2ኛ ደረጃ ነጭ ጤፍ 400 ኩንታል ጥራት ያለው አፈርና ደሸቅ የሌለው ንፁህ የሆነና ተቋሙ በሚያቀርበው የጤፍ ናሙና መሰረት ማቅረብ የሚችል፤ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

እንዲሁም የባቄላ ክክ 350 ኩንታል መሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

1. በዘመኑ የ2018 ዓ.ም የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና (የምትችል)

2. በግልጽ ጨረታ ከሚገዛውና ከሚሸጠው /ሰብል ጋር የተዛመደ ንግድ ሥራ ፍቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት(Value Added Tax Certificate)ተመዝጋቢ ከሆነ /የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት(Tax Payer identification number) እንዲሁም ሌሎች ለጨረታው የሚጠቅሙ ማስረጃዎችን የተገናዘበ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል (የምትችል )

3. ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ ከሚገዛው ጤፍና ከሚሸጠው የባቄላ ከከ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር በመከፈል ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 10 /አስር/ የሥራ ቀናት የጨረታ ሰነድ ሰቆጣ ከተማ ወይብላ ማርያም አጠገብ ከሚገኘው ቢሮ ቁጥር 1 በመምጣት መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

4. ተጫራቾች በሌላ ዋጋ ተመስርቶ መወዳደር የማይቻል መሆኑንና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው አሸናፊው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 5 ቀናት እንዲሁም የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (CPO) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል። ዋስትናው ውል ከተፈፀመበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 ቀናት ፀንቶ ሊቆይ የሚችል መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በተፈቀደላቸው በታወቁ ባንኮች ዋስትና (CPO) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታው ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ዋናውን የገቢ ደረሰኝ ከማወዳደሪያ ሃሳብ ጋር አብሮ ማስገባት ሲኖርባቸው በጨረታ ሰነዱ ከተቀመጠው ዝርዝር መግለጫ ውጪ መጨመርም ሆነ መቀነስ አይፈቀድም።

6. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው ከወጣበትን ቀን አንስቶ ለተከታታይ 10/ አስር / የሥራ ቀናት ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰነዱን በመግዛት የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በቀን አስራ አንደኛ ቀን / 3፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

7. የጨረታው ሰነድ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ዋቢ ሁለገብ የገ/ህ/ስ/ማ ኃላፊነቱ የተወሰነ ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ 10 የሥራ ቀናት ቆይቶ በ 11/አስራ አንደኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪል በተገኙበት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ታሽገው ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ጨረታው ይከፈታል። በጨረታ መክፈቻ ሥርዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታ አከፋፈት ባይገኙም በጨረታ አከፋፈት ሥርአት ተገዥ ይሆናሉ።

8. ተጫራቾች የጨረታ ማወዳደሪያ ሃሳባቸውን ለማሻሻል ወይንም ከጨረታው ለመውጣት የፈለጉ እንደሆነ የጨረታ ማወዳደሪያ ሀሳብ ለማቅረብ ከተሰጣቸው 3 ቀን /ሶስት ቀን በፊት/ በጽሑፍ ሊያሳውቁ ይገባል።

9. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡ ፡ ይህም ሲባል ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ላወጡት ወጪ መ/ቤቱ ኃላፊነት የማይወስድ መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

10. ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ዋግ ኸምራ ብሄረሰብ ዋቢ ሁለገብ የገ/ህ/ስ/ማህበር ኃላፊነቱ የተወሰነ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 440 1173 /0941 82 17 89/0933 214 815 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

በዋግ ኽምራ ሰቆጣ ከተማ የዋቢ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ዩንዬን ኃ/የተወሰነ


Tender details

  • Deadline: 2026-08-15
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ 10 የሥራ ቀናት ቆይቶ በ 11/አስራ አንደኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪል በተገኙበት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-15 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ 10 የሥራ ቀናት ቆይቶ በ 11/አስራ አንደኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪል በተገኙበት ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Wabi Farmers Cooperative Union
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 100 (አንድ መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 04, 2026)
  • Posted at: 2026-08-04T08:12:15.000Z
← Back to all tenders