Grains, pulses and staples
የጎዛምን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ነጭ ጤፍ፣ ምጥን በርበሬ፣ የባልትና ውጤቶች፣ ሸቀጣ ሸቀጥ እና የፊኖ ዱቄት ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጎዛምን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት አመት በጸጥታ ስራ ላይ ለተሰማሩ የሰላም አስከባሪ አካላት ለቀለብ አገልግሎት የሚውሉ ልዩ ልዩ ግብአቶችን
- ሎት 1. ነጭ ጤፍ፣
- ሎት 2. ምጥን በርበሬ፣
- ሎት 3. የባልትና ውጤቶች፣
- ሎት 4. ሸቀጣ ሸቀጥ፣
- ሎት 5. የፊኖ ዱቄት ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸውና ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ።
- በመመሪያ ከቫት ነፃ ከተደረጉ ገዥዎች ውጭ ያሉትን የግዥ መጠናቸው ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ) ብር እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት ኮፒውን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈልና የጨረታ ሰነዱን ጎዛምን ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 8 ማግኘት ይችላሉ።
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በእያንዳንዱ ሎት ተጫራቾች የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በማለት በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገm ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ጋራንቲ ከጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት ገቢ ማድረግ ይኖርበታል። በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ለዋና ገንዘብ ያዥ በመሂ-1 ገቢ አድርጐ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ሲፒኦ ብሎ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ መክፈቻ ቀኑን በተመለከተ ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት እስከ 11፡30 ድረስ የጨረታ ስነዱ ሲሸጥ ይቆይና በ16ኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ በ4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድኑ ተዘጋጅቶ የተሠጣቸውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ የይዘት ለውጥ ወይም ማሻሻያ ሳያደርጉ ሞልተው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ሆኖም የተሠጠው ሰነድ ላይ የግልጽነት ማብራሪያ ካስፈሰገ ደውለው ወይንም በአካል ቀርበው መጠየቅ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሠነዳቸውን በእያንዳንዱ ገፅ ላይ ፊርማቸውንና ማህተም በማድረግ በፖስታ በማሸግና ፖስታው ላይ አድራሻ በመፃፍ ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 8 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚገዙ ዕቃዎችን ዝርዝር መግለጫ በግዥ ቡድናችን ከተዘጋጀው መደበኛ የጨረታ ሠነድ ላይ ማየት ይችላሉ። ለሚገዙ ገዥዎች ናሙና የግዥ ቡድናችን ቢሮ ላይ የሚቀመጥ ይሆናሉ።
- ግዥ ፈፃሚው መ/ቤት የጨረታ ውድድሩን በሎት ዋጋ ወይም በጥቅል ዋጋ ድምር የሚያወዳድር ሲሆን ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች አሸናፊ ሆኖ የሚመረጥ ይሆናል።
- ዕቃ አቅርቦት ጥራት ችግር እንዳይከሠት በሚመለከታቸው ባለሙያዎች ለተረጋገጡ የዕቃዎች ርክክብ የሚፈፀም ይሆናል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 40 ቀን ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 178 0130/058 771 1422 መደወል ይችላሉ።
የጎዛምን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-11
- Bid closing time: 09:30
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-11 10:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: East Gojam Zone Gozamen F/E/D/Bureau
- Bid bond: 1% በእያንዳንዱ ሎት
- Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Published on: Be'kur (Jul 27, 2026)
- Posted at: 2026-07-29T06:05:17.000Z