የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ቅርንጫፍ 3 ጽ/ቤት የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን፣ ቆርቆሮዎች፣ ንቃይ የብረት በርና መስኮቶች፣ የሕንጻ መሳሪያዎች፣ የጽኅፈት መሳሪዎች እና የተለያዩ የቢሮ እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- ቅ/3/ን/ማስ/ግ/ጨ/ሽያጭ001/2018
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ቅርንጫፍ 3 ጽ/ቤት እስቶር የሚገኙ
በሎት 1 ኪሎ የሚሸጡ የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን ቆርቆሮዎች ንቃይ የብረት በርና መስኮቶች ቆርቆሮዎችን በሎት 2 በጥቅል ዋጋ የሚሸጡ የሕንጻ መሳሪያዎች የጽኅፈት መሳሪዎች አገልግሎት ሰጥተው ተመላሽ የተደረጉ የቢሮ እቃዎች( ወንበሮች ጠረጴዛዎች ኮምፒውተሮች ካሜራ እና እስካነር ዩፒኤስ ኤሌክትሪኒክሶች እና ንቃይ የእንጨት በሮችን ሌሎች አሮጌ እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ እና የቫት ተመዝጋቢዎች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን፦
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን መስቀል ፍላወር መንገድ ድሪምላይነር ሆቴል ጀርባ ወረዳ 2 አይሻ መስጂድ አጠገብ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ቅርንጫፍ 3 ዕ/ቤት በመምጣት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ከፍል 7 በዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ ስር የሚገዙበትን ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታከስ ጨምሮ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ በቅርንጫፍ 3 ፅ/ቤት ግዢና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት 11፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች በሎት 2 በጥቅል የመነሻ ዋጋ ከተቀመጠላቸው እቃዎች መካከል የሚፈልጋቸውን እቃዎች ብቻ መርጦ ዋጋ መስጠት አይችሉም።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ሎት1 : በኪሎ ለሚሸጡ እቃዎች ብር 50.000.00 (ሀምሳ ሺህ) ለሎት 2 በጥቅል ለሚወዳደሩበት እቃዎች ብር 25,000.00 (ሀያ አምስት ሺህ) የጨረታ ማስከበሪያ በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ቅርንጫፍ 3 ፅ/ቤት ስም በተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሳጥኑ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ ክፍት ሲሆን በ10ኛው ቀን 11፡30 ሰአት ታሽጎ በ11ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቅርንጫፍ 3 ዕ/ቤት የግዢ እና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ይከፈታል። ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ተጫራቾች ሳይገኙ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም።
- የጨረታ መክፈቻ ቀን እሁድ ወይም በበዓል ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
- በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ለሎት 1 በኪሎ ለሚሸጡ እቃዎች ብር 200,000.00( ሁለት መቶ ሺህ ) ቅድመ ክፍያ በመክፈል ለሎት 2 በጥቅል ለሚሸጡ እቃዎች እቃው እንደተቆጠረ ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃላይ መክፈል ይኖረባቸዋል። ሆኖም ሙሉ ክፍያው በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካላቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ይደረጋል ።
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን እቃ በሙሉ በ5 ቀናት በራሳቸው ጉልበት ሠራተኛና ትራንስፖርት አቅርበው አስጭነው መውሰድ ግዴታ አለባቸው። እቃዎቹን በወቅቱ ካላነሱ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 0.001% በየቀኑ እየተሰላ በመቀጫነት እንዲከፍሉ ይደረጋል። ሆኖም የመቀጫው መጠን የጠቅላላውን ዋጋ 10% ሲደርስ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለኮርፖሬሽኑ ገቢ ተደርጎ አሸናፊነቱ ይሰረዛል።
- በሎት 2 ሽያጭ ከቀረቡ እቃዎች ዝርዝር ውስጥ ጉድለት የሚገኝ እቃ ካለ ከጠቅላላው መነሻ የዕቃው ነጠላ ዋጋ ለአሸናፊው ተቀናሽ የሚደረግለት ሲሆን በዚህ ምክንያት ከጎደለው እቃ በከፊልም ሆነ በሙሉ እቃውን ያለመረከብ መብት የለውም።
- በተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥሮች - /09-12-02-29-13 ይደውሉ።
- ቅርንጫፍ 3 ጽ/ቤት ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ቅርንጫፍ 3 ፅ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-05-30
- Bid closing time: 17:30
- Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ ክፍት ሲሆን በ10ኛው ቀን 11፡30 ሰአት
- Bid opening: 2026-06-01 10:30
- Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ ክፍት ሲሆን በ10ኛው ቀን 11፡30 ሰአት ታሽጎ በ11ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Housing Corporation
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published: May 20, 2026
- Posted at: 2026-05-20T09:24:00.000Z
- Buyer website: https://www.fhc.gov.et
Documents
Categories
Other SalesSales, Disposals and ForeclosureDisposal SaleAluminium ProductsSteel, Metals and AluminiumSteel Raw Materials and ProductsOther MetalsMetal and Metal WorkingBuilding and Finishing MaterialsConstruction and Water WorksStationeryOffice Supplies and ServicesAudio Visual, Photography and Filming Service and EquipmentArtEquipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsComputer and AccessoriesIT and TelecomOffice Machines and AccessoriesHouse FurnitureFurniture and FurnishingOffice FurnitureWood and Wood WorkingAmharic2merkatoFederal Housing CorporationAddis Ababa
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.