ቡሳ ጎኖፋ ማይክሮፋይናንስ አክስዮን ማህበር በድርጅቱ የሚገኙን ያገለገሉ ቋሚ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ቋሚ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ የተዘጋጀ

ቡሳ ጎኖፋ ማይክሮፋይናንስ አክስዮን ማህበር በድርጅቱ የሚገኙን ያገለገሉ ቋሚ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ስለዚህ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

1. ተጫራቾች ጠመንጃ ያዥ አካባቢ በሚገኘው ዋና መስሪያ ቤታችን በቤተ ሰኢዳ ህንጻ 4ኛ ፎቅ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ቢሮ በመምጣት የጨረታውን መረጃ፤ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ ከፍለው መወሰድ ይችላሉ።

2. ተጫራቾች ስነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀናት ከቀኑ 8፡00 እስከ 10:00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ለሽያጭ የቀረቡ ንብረቶችን በድርጅታችን ዋና መስሪያ ቤት መጋዘን እና ሞጆ በሚገኘው ቅርጫፍ ጽ/ቤታችን በአካል በመገኘት መመልከት ይችላሉ። የኮምፒተር እና ፕሪንተር እቃዎች የሚገኙት በዋናው መ/ቤት ክፍል ሲሆን የተቀሩት እቃዎች የሚገኙት ሞጆ በሚገኘው ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ግዜያዊ መጋዘን ውስጥ ነው።

3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለያንዳንዱ ምድብ ለሚያቀርቡት 20% (ፐርሰንት) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝና በታሸገ  ኤንቬሎፕ በማድረግ በድርጅታችን የንብረት ክፍል ለዚሁ ስራ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።

4. የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋ እና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ( ሲፒኦ) እንዲሁም በጨተታው የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ነው።

5. ከላይ በተራ ቁጥር 4 የተገለጸውን የጨረታ ማከበሪያ ዋስትና ያላስያዘ እና በሰነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል።

6. የጨረታ ሰነዱ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ላሉት 10 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን፤ በ10ኛው ቀን ማለትም ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ በ6፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም  ህጋዊ ወኪሎቻችው በተገኙበት በድርጅታችን የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል። ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጫረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉለውም።

7. በጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች የአሸነፊዎች ዝርዝር በመስሪያ ቤቱ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር ከ3 /ሶስት/ ተከታታይ የስራ ቀናት ብኋላ ባሉት 2/ሁለት/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የውል ማስረከቢያ የውል ዋጋውን 10 በመቶ በማቅረብ ከድርጅቱ ጋር ውል መፈራረም ይኖርባችዋል። ሆኖም ከላይ በተገለጸው መሰረት ውል ላልፈረሙ ወይም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከቢሪያ ለድርጅቱ ገቢ ምድብ ይደረጋል።

8. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ንብረት በራሳቸው ወጭ በማጓጓዝ ውል በተፈረመ በ10 የስራ ቀናት ውስጥ በማንሳት ማጠናቀቃቸው ሲረጋገጥ ያስዙት የጨረታ ማስከበሪያ ተማላሽ ይደረግላቸዋል።

9. ድርጅቱ ባወጣው ጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል።

10. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈከገ በስልክ ቁጥር 011 416 2536፤ 09 36 78 48 33 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

11. ድርጅቱ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማንኛውም ጊዜ ጨረታውንም ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ምድብ 1. የኮምፒተር እና ፕሪንተር እቃዎች

ተ.ቁ

የእቃዉ አይነት

መለኪያ

ብዛት

1

የኮምፒዩተር ሞኒተር

በቁጥር

9

2

የኮምፒዩተር ኪ ቦርድ

25

3

ኤችፒ ሌዘርጀት ፕሪንተር

14

4

ዴስክ ቶፕ ሲ ስተም ዩኒት

23

5

ላፕ ቶፕ ኮምፒተር

20

6

የኮምፒዩተር ስፒከር

8

7

የኤች ዲ ኤም አይ ገመድ

2

8

ኮፒ ማሽን ካኖን 2202

1

9

የዉሃ ማጣሪያ

2

10

ጠረጴዛ የኮፒ ማሽን ማስቀመጫ

1

 ምድብ 2. ጀነሬተሮች

ተ.ቁ

የእቃዉ አይነት

መለኪያ

ብዛት

1

ካማ ጀነሬተር

ቁጥር

3

2

ሮቢን ጀነሬተር

ቁጥር

5

ምድብ 3 ፌሮ ብረት እና ብረታ ብረት እቃዎች

ተ.ቁ

የእቃዉ አይነት

መለኪያ

ብዛት

1

የብረት መስኮት ባለ መስታወት

በቁጥር

2

2

የብረት በር ባለ መስታወት

በቁጥር

1

3

የመስኮት ፍርግርግ ብረት

በቁጥር

1

4

ፌሮ ብረት ( ባለ 10፤ እና ባለ 12 በቁጥር

በቁጥር

29

5

የአጥር ሽቦ ባለ እሾህ

በጥቅል

በጥቅል

6

የውሃ ቱቦ ብረት

በቁጥር

4

7

ስታፋ ብረት

በጥቅል

በጥቅል

8

ያረጁና ቁርጥራጭ ቆርቆሮዎች

በቁጥር

 

9

ታፔላ ብረት

በቁጥር

2

10

የብረት በር

በቁጥር

3

11

የብረት መስኮት

በቁጥር

1

12

አሮጌ ቱቦላሬ

በቁጥር

14

13

የከተም በር

በቁጥር

1

 ምድብ 4. ፕላስቲክ ነክ እቃዎች

ተ.ቁ

የእቃዉ አይነት

መለኪያ

ብዛት

1

ፕላስቲክ ቆርቆሮዎች

በቁጥር

2

2

ፒፒሲ ጆይንት ባለ 110

በቁጥር

11

3

ፒፒሲ ሙሉ

በቁጥር

4

4

ፒፒሲ 1/2 (ግማሽ)

በቁጥር

4

5

የኮርኒስ መስሪያ ፕላስቲኮች

በጥቅል

15

ምድብ 5. እንጨት እና እንጨት ነክ እቃዎች

ተ.ቁ

የእቃዉ አይነት

መለኪያ

ብዛት

1

የእንጨት መስኮት

በቁጥር

3

2

የእንጨት መስኮት ባለ መስታወት

በቁጥር

2

3

የእንጨት መስኮት ባለ ፌሮ ፍርግርግ ብረት

በቁጥር

1

4

የእንጨት በር

በቁጥር

8

5

የእንጨት ሞራሌ

በጥቅል

3

6

ጣውላ

በቁጥር

1

7

የተሰባበሩ እንጨቶች

በጥቅል

8

አድራሻ፡ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ ፊት ለፊት ቤተ ሰኢዳ ህንጻ 4ኛ ፎቅ አስተዳደር መምሪያ ቢሮ (አ.አ.) ስልክ ቁ. 011 416 2621/ 09 36 78 48 33


Tender details

  • Deadline: 2026-05-29
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid opening: 2026-05-29 15:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Busa Gonofa Micro Finance S.C
  • Bid bond: ለያንዳንዱ ምድብ ለሚያቀርቡት 20% (ፐርሰንት)
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: May 20, 2026
  • Posted at: 2026-05-20T11:31:25.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders