ግሎባል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ. በቦሌ መንገድ ከሱር ኮንስትራክሽን ዋና መ/ቤት ገባ ብሎ ወይም ከዲቦራ ፋውንዴሽን አጠገብ ያስገነባውን (2B+G+9) ለቅይጥ አገልግሎት የሚውል ሕንፃ ማከራየት ይፈልጋል
Description
የሕንፃ ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ
ግሎባል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ በቦሌ መንገድ ከሱር ኮንስትራክሽን ዋና መ/ቤት ገባ ብሎ ወይም ከዲቦራ ፋውንዴሽን አጠገብ ያስገነባውን (2B+G+9) ለቅይጥ አገልግሎት የሚውል ሕንፃ
- ለንግድና ለቢሮ የምድር ወለል እና እስከ 2ኛ ወለል
- ለአፓርትመንት (መኖሪያ) ከ3ኛ ወለል እስከ 9ኛ ወለል ድረስ ማከራየት ይፈልጋል
ሕንፃው የተሟላ የፓርኪንግ፣ የኤሌትሪክ ኃይል፣ የውሀ አቅርቦት እና የኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ያለው ሲሆን ለቢሮና እና ለንግድ የሚውሉ የሕንፃው ሙሉውን ወይም እንደምርጫው በከፊል ለማከራየት ይፈልጋል።
በመሆኑም የተጫራጮች ሕንፃው በሚገኝበት ቦታ ዘወትር በሥራ ሰዓት በአካል ተገኝቶ በማየት ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ.ም. ሱማሌ ተራ በሚገኘው የኩባንያው ዋና መ/ቤት 5ኛ ፎቅ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
1. ተጫራቾች በተጠቀሰው አድራሻ ለጨረታ ማስገቢያ የተዘጋጀው ቅፅ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
2. ተጫራቾች ያስገቡት ሰነድ ግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ላይ የሚከፈት ሲሆን በጨረታው ላይ ለመገኘት በፈለጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ጨረታው በሚከፈትበት ሰዓት መገኘት ይችላሉ።
3. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ ግሎባል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ በአካል በመቅረብ ወይም
በስልክ ቁጥሮች 0111 56 74 00/ 0111 56 58 50 /0111 56 58 53 ደውለው ማግኘት ይችላሉ።
Tender details
- Deadline: 2026-05-30
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-05-30 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Global Insurance S.C.
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: May 20, 2026
- Posted at: 2026-05-20T12:02:40.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.