Stationery and office consumables
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የሳንጃ ሆስፒታል ለ2018 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የሳንጃ ሆስፒታል ለ2018 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ
- ሎት 1. የፅህፈት መሳሪያ፣
- ሎት 2. የፅዳት እቃዎች፣
- ሎት 3. አልባሳት፣
- ሎት 4.የመኪና ጎማ፣
- ሎት 5. የቧንቧ እቃ፣
- ሎት 6. የኤሌክትሪክ እቃ ፣
- ሎት 7. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል።
የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው።
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የሚገዙ አይነትና ዝርዝር መግለጫ (እስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰአት በሳንጃ ሆስፒታል ግ/ፋ/ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ወይም ሲ.ፒኦ ማስያዝ አለባቸው ወይም በጥሬው ማስያዝ ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ ለየብቻ በመለየት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ከግንቦት 10/2018 ዓ.ም እስከ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ጀምሮ መውሰድና መመለስ የሚችሉ ሲሆን በ16ኛው ቀን ግንቦት 25/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሳንጃ ሆስፒታል የስብሰባ አዳራሽ በግልፅ የሚከፈት ይሆናል።
- አሸናፊው የሚለየው በሎት ወይም በጥቅል እቃ ዋጋ ሲሆን መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በነጠላ ዋጋ አሸናፊውን የመለየት መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አሸናፊው ድርጅት ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ታች አር/ወረዳ ዐ/ህግ ጽ/ቤት ቀርቦ ውል መውሰድ የሚችልና እቃዎችን ሳንጃ ሆስፒታል ባለው የንብረት መጋዝን በዝርዝር ማስረክብ የሚችል መሆን አለበት።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 18 19 85 88 ወይም 09 39 24 50 07 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
- አሸናፊው እቃውን ማቅረብ ያለበት በጨረታ ሰነዱ ላይ የተሰጠውን ሞዴል እንጅ ስርዝ ድልዝ ወይም ሌላ ተመሳሳይ እቃዎችን ማቅረብ አይቻልም።
- ከጨረታ ሰነዱ ላይ ከተቀመጠው የዋጋ ሞሙያ ፎርም በስተቀር በማሰባሰቢያ የሚሞሉ የዋጋና የሞዴል መረጃን የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን።
- መ/ቤቱ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 10በመቶ ማስያዝ የሚችሉ መሆን አለበት።
- አሸናፊው መስሪያ ቤቱ በሚያቀርበው ናሙና መሰረት ማስረከብ የሚችል መሆን አለበት።
የሳንጃ ሆስፒታል
Tender details
- Deadline: 2026-06-02
- Bid closing time: 09:30
- Bid opening: 2026-06-02 10:00
- Region: Amhara
- Publishing entity: የሳንጃ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Published on: Be'kur (May 18, 2026)
- Posted at: 2026-05-21T08:11:07.000Z