በደቡብ ጎንደር አስተዳደር የሊቦ ከምከም ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለሊቦ ከምከም ወረዳ አስተዳዳር ጽ/ቤት ለግንባታ እቃዋች አገልግሎት የሚውሉ የኮንስትራክሽን እቃዎች፣ ስሚንቶ ቲፔስ ከተጫራቾች መካከል በማወዳደር በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ጎንደር አስተዳደር የሊቦ ከምከም ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለሊቦ ከምከም ወረዳ አስተዳዳር ጽ/ቤት ለግንባታ እቃዋች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. የኮንስትራክሽን እቃዎች፣ ሎት 2. ስሚንቶ ቲፔስ ከተጫራቾች መካከል በማወዳደር በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።
1. የቲን ተመዝጋቢ የሆኑ።
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉና ፈቃዱን ያደሱ።
3. የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረት ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
5. የሚገዙ ዕቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ሊቦ ከምከም ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ማግኘት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሎት 1. ብር 30,000 (ሰላሳ ሽህ ብር) ብቻ ሎት 2. ብር 30,000 (ሰላሳ ሽህ ብር ሽህ ብር) ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ የሚያስይዙ ከሆነ የገቢ ደረሰኝ መቁረጥ እና ከሰነዱ ጋር ኮፒ መያያዝ አለባቸው።
8. የጨረታ ሰነዱ የሚሸጥበት በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለተከታታይ ለ15 ቀናት እስከ 11፡30 ይቆያል።
9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ሊቦከምከም ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ንብ/አስ/ድን መሪ ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን የጨረታው ማስከበሪያውን ከኦርጅናል ሰነዱ ፖስታ ውስጥ በማድረግ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከተዘጋጀው ሳጥን እስከ 15 ኛው ቀን ድረስ እስከ 11፡30 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በ15ኛው ቀን 11፡30 ላይ ይታሸጋል።
10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ወቅት ባይገኝ የጨረታውን መክፈት የማያስተጓጉለው ከመሆኑም በተጨማሪ በጨረታ ሂደቱ ለተላለፉ ውሳኔዎች ተገዥ ይሆናሉ፡፡ 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
11. አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ማስያዝ አለባቸው።
12. መ/ቤቱ ከሚገዛው እቃ ግዥ ላይ 20 ከፍና ዝቅ የማድረግ መብቱ የተጠበቀ ነው።
13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
14. አሸናፊው የሚለየው በጥቅል ነው።
15. አሸናፊው ያሸነፈውን እቃ ሊቦከምከም ወረዳ አስተዳዳር ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ ማድረስ አለበት።
16. ጨረታው ሥርዝ ድልዝ ሳይኖረው እና እንዲነበብ ተድረጎ መሞላት አለበት።
17. አሸናፊው ተጫራች ሁሉም ሎቶች በተጠየቁት ጥራት (ስፔስፊኬሽን) መሰረት በባለሙያ ተፈትሾ ማሰረከብ የሚችል።
18. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በአካል በመገኙት ወይም በስልክ ቁጥር 058 444 01 95 /931 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
የሊቦ ከምከም ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-01
- Bid closing time: 17:30
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን 11፡30
- Bid opening: 2026-06-02 12:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00
- Region: Amhara
- Publishing entity: Libo Kemkem Woreda F/E/D/Bureau
- Bid bond: ለእያንዳንዱ ሎት 30,000 (ሰላሳ ሽህ ብር)
- Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ ሰነድ
- Published: May 18, 2026
- Posted at: 2026-05-21T08:13:50.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.