Property and building foreclosure

የባንጃ ወረዳ ፍርድ ቤት የድርጅት ቤት የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ አውጥቷል

Description

የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

በአፈ/ከሳሽ አቶ አዝመራው ዳኛው እና በአፈ/ተከሳሽ እነ ይቻላል ምናየ መካከል ባለዉ ገንዘብ ክርክር ጉዳይ በእንጅባራ ከተማ 05 ቀበሌ በአዋሳኝ በምሥራቅ መሰረት ቸኮለ፣ በምዕራብ ገረመው ታመነ፣ በሰሜን መንገድ እንዲሁም በደቡብ ሀብታሙ መኮነን መካከል የሚያዋስነውን በአፈ/ተከሳሽ በወ/ሮ በላይነሽ ብዙየ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ የድርጅት ቤት በመነሻ ዋጋ ብር 2,258,769,40 (ሁለት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሃምሳ ስምንት ሺህ ሰባት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ብር ከአርባ ሳንቲም) ስለሚሸጥ የጨረታ ማስታወቂያ ለ30 ተከታታይ ቀናት ማለትም ግንቦት 10/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 10/2018 ዓ.ም ድረስ በተከታታይ 30 ቀናት ቆይቶ ሰኔ 11/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 እንዲሸጥ ሲል ፍ/ቤቱ አዝዟል።

ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ወደ ጨረታው ስትመጡ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/4 ኛውን (በሲፒኦ) ይዛችሁ እንዲቀርቡ እናሳስባለን።

የባንጃ ወረዳ ፍርድ ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-18
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid opening: 2026-06-18 12:00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Banja Woreda Court
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Be'kur (May 18, 2026)
  • Posted at: 2026-05-21T08:17:00.000Z
← Back to all tenders