ፀደይ ባንክ ደሴ ዲስትሪክት የቦታው ስፋት 1698.43 ካ.ሜ የሆነ ለሆቴልና ቱሪዝም የሚውል ህንፃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

ፀደይ ባንክ ለአቶ ሽመልስ አማረ ቀወይ ለሰጠው ብድር በመያዣ ያስያዘውን በደሴ ከተማ ቀበሌ 10 የካርታ ቁጥር LHC AM003023716012 የቦታው ስፋት 1698.43 ካ.ሜ የሆነ ለሆቴልና ቱሪዝም የሚውል ህንፃ በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታው ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች በመገንዘብና ቅድመ ሁኔታዎችን በማሟላት መጫረት ይችላሉ።

1. የቤቱ የጨረታ መነሻ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን ሳይጨምር ግምቱ 52,138,130.33 (ሃምሳ ሁለት ሚሊዮን አንድ መቶ ሰላሳ ስምንት ሽህ አንድ መቶ ሰላሳ ብር ከሰላሳ ሶስት ሳንቲም) በሆነ ይጫረታል።

2. ተጫራቾች የቤቱን የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 1/4ኛውን በጥሬ ገንዘብ ወይም (በሲፒኦ) በፀደይ ባንክ አማ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

3. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱን የሚያረጋግጠው የጨረታው ውጤት በሚመለከተው አካል ፀድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጣቸው ብቻ ነው።

4. በጨረታው የሚሳተፈው በህግ ሰዉነት ያገኘ ከሆነ የድርጅቱ መመስረቻ ጽሁፍ ወይም መተዳደሪያ ደንብ ህጋዊ ሰውነት ያገኘበት የምዝጋባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ህጋዊ ውክልና ማቅረብ አለባቸው።

5. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱን በባንኩ ደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ10 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈልና በጨረታ ያሸነፈውን ንብረት መረከብ ይኖርበታል፡፡ አሸናፊው በ10 ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።

6. በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ጥሬ ገንዘብ ወይም ሲፒኦ ይመለስላቸዋል።

7. የጨረታ አሸናፊው ከሚገዛው ንብረት ዋጋ በተጨማሪ ከቤቱ ጋር የተያያዘ ማንኛውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች ግብር፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ 15 በመቶ እና ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማንኛውንም ወጭዎች ገዥ ይሸፍናል (ይከፍላል)፣ ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ በባንኩ የሚከፈል ሆኖ ለቀረው የክፍያ ጊዜው ያልደረሰ የሊዝ ክፍያ ገዥ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር እንዲዋዋል ይደረጋል።

8. ተጫራቾች ቤቱን (ድርጅቱን) በባንኩ አማካኝነት መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ።

9. ጨረታው የሚካሄደው ሰኔ 13/2018 ከጠዋቱ 3፡00 እሰከ ቀኑ 6፡00 በደሴ ከተማ መናፈሻ በሚገኘው ፀደይ ባንክ ደሴ ዲስትሪክት ግቢ ዉስጥ ግልጽ በሆነ ጨረታ የሚከናወን ይሆናል፡፡ አሸናፊዉ አሸናፊነቱን የሚያረጋግጠዉ ከላይ በተራ ቁጥር 3 ላይ በተገለፀዉ አግባብ ደብዳቤ ሲደርሰዉ ነዉ።

10. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11. ለተጨማሪ መረጃ ፀደይ ባንክ ደሴ ዲስትሪክት በስልክ ቁጥር- 033 312 64 74 /033 111 82 72 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ።

ፀደይ ባንክ ደሴ ዲስትሪክት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-20
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid opening: 2026-06-20 12:00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Tsedey Bank S.C.
  • Buyer address: Legahar Orda Building, 8th Floor room No-804
  • Bid bond: 25%
  • Published: May 18, 2026
  • Posted at: 2026-05-21T08:25:07.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders