የዳንግላ ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት ለመኖሪያ እና ለድርጅት አገልግሎት የተዘጋጁ ቦታዎችን 3ኛ ዙር በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል
Description
የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
የዳንግላ ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት የመሬት ማስተላለፍ ቡድን የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 መሠረት ለመኖሪያ እና ለድርጅት አገልግሎት የተዘጋጁ ቦታዎችን 3ኛ ዙር በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡-
- ጨረታው ከግንቦት 10/2018 ዓ/ም ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ይቆያል፡፡
- የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና ለጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ዳንግላ ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት የመሬት ማስተላለፍ ቡድን ቢሮ ቁጥር 07 ድረስ በመምጣት ዘወትር በስራ ስዓት ሰነድ መግዛት እና መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ እና መሸጫ ጊዜ ግንቦት 10/2018 ዓ/ም ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋው 10 የስራ ቀናት ተቆጥረው በ10ኛው ቀን 11፡00 ሁሉም የጨረታ አስፈፃሚ ቡድን አባላት እና አግባብ ያለው አካል የሚሰይማቸውን ታዛቢዎች በተገኙበት ይሆናል፡፡
- ቦታውን መጎብኘት ለሚፈልጉ ተጫራች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገለፀው መርሃ ግብር መሠረት የምናስጎበኝ ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው ዝግ ከተደረገበት ቀን በኋላ ባለው የመጀመሪያ የስራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአገው ምድር አዳራሽ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ በዳንግላ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ ቦታዎች በሚለጠፋ ማስታወቂያዎች እና ቢሮ ቁጥር 06 ወይም በስልክ ቁጥር 058 221 07 72 /058 221 19 83 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የዳንግላ ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-05-28
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ጨረታው የሚዘጋው 10 የስራ ቀናት ተቆጥረው በ10ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-29 10:00
- Bid opening (note): ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው ዝግ ከተደረገበት ቀን በኋላ ባለው የመጀመሪያ የስራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Dangela City Administration Urban Development & Land Development Bureau
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: May 18, 2026
- Posted at: 2026-05-21T09:05:17.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.