የሆሳዕና ከተማ አስ/ር ማዘጋጀ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች (ለንግድ) የተዘጋጀ ቦታን በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል

Description

የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

1. የጨረታው ዙር፡- 3ኛ

2. የጨረታ ዓይነት፡- መደበኛ

3. በሀዲያ ዞን የሆሳዕና ከተማ አስ/ር ማዘጋጀ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 በፊደል ተራ ከሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሠረት ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች (ለንግድ) የተዘጋጀ ቦታን በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል። በመሆኑም መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ለመኖሪያ 600 /ስድስትመቶ/ ብር ለንግድ 800/ ስምንት መቶ/ ብር በመክፈል ከማዘጋጀ ቤቱ መሬት ልማትና ማናጅመንት ዘርፍ ቢሮ ቁጥር 3 እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ብቻ መግዛት የሚቻል መሆኑን እናስታውቃለን። ለመደበኛ ጨረታ በ10ኛው ቀን የጨረታ ሰነድ የሚሸጠው እስከ 9፡00 ሰዓት ብቻ ነው።

4. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመደበኛ 10/አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት እስከ ቀኑ 1፡00 ሰዓት ብቻ ይሆናል።

5. የጨረታው ሳጥን የሚታሸገው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣበት 10 ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ይሆናል።

6. ቦታውን መጎብኝት ለሚፈልግ ተጫራች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገለጸው መርሀ ግብር መሠረት የምናስጎበኝ ይሆናል።

7. ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣበት በ11ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በሆሳዕና ከተማ አቢዮ ኤርሳሞ ስታዲየም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል። 11ኛውና ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።

8. ስለ ጨረታው ዝርዝር ማብራሪያ ከጨረታው ሰነድ ማግኘት ይቻላል።

9. ማዘጋጃ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከሆሳዕና ከተማ አስተዳደር www.hosannaca.gov.et  ማግኘት ይቻላል።

ተጨማሪ መረጃ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች ደውሉ ማግኘት ይቻላል።
046-555-3645
046-555-2355
046-555-2310
የሆሳዕና ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገ/ቶች ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-02
  • Publishing entity: ሆሳዕና ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች ጽ/ቤት
  • Bid document price: ለመኖሪያ 600 (ስድስት መቶ) ብር፣ ለንግድ 800 (ስምንት መቶ) ብር
  • Published: May 22, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders