በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የጽ/መሳሪያ፣ የውሃ እቃ፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃ እና የፕሪንተር ቀለም በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው ሴከተር መ/ቤቶች ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ
- 1ኛ የጽ/መሳሪያ 12000 ብር
- 2ኛ ውሃ እቃ 7000ብር
- 3ኛ የኤሌክትሮኒክስ እቃ 15000 ብር
- 4ኛ የፕሪንተር ቀለም 4000 በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታ እንድሳተፉ ይጋብዛል።
1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ቲን/ እንድሁም በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ድምር ከብር 200000/ ሁለት መቶ ሺህ ብር /በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢነት ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ።
2. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ የጨረታ ሰነድ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ የማይመለስ 300/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው የነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ሞልተው ኮፒና ኦርጅናል ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የጠቅላላ ዋጋ በዝርዝር ተሞልቶ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከላይ በተዘረዘረው ሎት የገንዘብ መጠን የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ ሲ.ፒ.ኦ/C.PO/ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በጥሬ ገንዘብ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቹ በዋጋ መሙያ ሰነድ ላይ ስም ፊርማና ማህተም በማድረግ በታሸገ ፖስታ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛ ቀን 3፡30 ድረስ በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለጨረታ በተዘጋጀ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. የጨረታ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ዕቃውን በሚ/ወ/ወ/ሴክተር መ/ቤቶች ባሉት ንብረት ክፍል ውስጥ ማድረስ ይኖረባቸዋል።
7. የጨረታ ውድድሩ እንደአስፈላጊነቱ በነጠላ ዋጋ ወይም በሎት ሊሆን ይችላል።
8. ጨረታው ተጫራቾች በአካል ሆነ ህጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት ወይም ባልተገኙበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡00 በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር18 ይከፈታል። የመክፈቻ ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ላይ የጨረታ ሰነድ የመጨረሻ ማስገቢያ ከጠዋቱ 3፡30 ሆኖ ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ጨረታው ይከፈታል።
9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስ/ቁ 011 117 0171 ወይም 09 13 57 44 40 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-06
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30
- Bid opening: 2026-06-06 12:00
- Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00
- Region: Amhara
- Publishing entity: Meda Weremo Woreda Finance and Economic Development Bureau
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300 (ሶስት መቶ ብር)
- Published: May 22, 2026
- Posted at: 2026-05-22T07:31:24.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.