የቤት የሐራጅ ሸያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሸያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት አለምነሽ አስፋው እና የፍ/ባለዕዳ ታምረስላሴ ኤልያስ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌ/ከ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁጥር 331627 በ03/10/2016 ዓ.ም እና የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁጥር 118233 በቀን ሚያዚያ 01 ቀን 2018 ዓ.ም በኮ/መ/ቁጥር 118233 በቀን 07/08/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 02 ውስጥ የሚገኝ ብሎክ 07 የቤት ቁጥር 24 ስፋቱ 64.04 ካ.ሜ በፍ/ባለዕዳ ስም ተመዘገቦ የሚገኝ ባለ 3 መኝታ የሆነው ኮንዶሚነየም ቤት የመለያ ቁጥር AA000080204158BA070324 የተመዘገበ ካርታ ያለው የሐራጅ መነሻ 2,668,674,88 (ሁለት ሚሊዮን ስድስት መቶ ስልሳ ስምንት ሺህ ስድስት መቶ ሰባ አራት ከ88/100) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል።የተጫራቾች ምዝገባ በ8፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤጽ/ስም CPO አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፤ በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በሕጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዞወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-23
- Bid closing time: 14:30
- Bid opening: 2026-06-23 14:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት
- Bid bond: 25%
- Published: May 22, 2026
- Posted at: 2026-05-22T07:37:34.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.