የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በ21/09/2018 በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ 100 (መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክሎት በማድረግ ለጨረታ የቀረቡትን የእቃዎችን ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየትና እና በማረጋገጥ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው መሳተፍ የሚቻል ሲሆን የእቃዎችን ሳምፕል ከቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ከአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት እና በቴሌግራም ማየት የሚቻል መሆንንና ወደ ቃሊቲ እንዲመጣሎት የምትፈልጉት የእቃ ናሙና ካለ የጨረታ ማስታወቂያ በወጣበት ቀን በስልክ ቁጥር 022-24-1402 በመደወል ወደ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት እንዲመጣሎት ማድረግ የምትችሉመሆኑን እናሳውቃለን።

የጨረታ መስፈርቶች ፡-

1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ መሳተፍ የሚያስፈልጉ ተጫራች በጨረታ በሚሸጡ ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርትፍኬት የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለ መሆኑ ክሊራንሰ (Clearance) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴያቸውን ለታክስ ማዕከሉ ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና የመለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር እያይዞ ማቅረብ የሚችል። 

2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀን በ21/09/2018 ዓ/ም እስከ ጠዋቱ 3፡45 የእቃውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ አዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ 100(መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክሎት ማድረግ ይችላሉ።

3. ለግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋሰትና (cpo) የሚወዳደሩበት እቃ ኮድ 5 በመቶ እንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩበት እቃ ኮድ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ አሰርተው በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

4. ተጨራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (እስኬጁል) መሰረት በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በመገኘት መጫረት ይችላሉ።

.

 

የጨረታው ቦታ

 

የጨረታ ዓይነት

 

ለጨረታ የቀረቡ እቃዎች

 

የዕቃዎች መመልከቻ ቀን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ

የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት

 

1

ቃሊቲ /// ቤት

 

ግልጽ ጨረታ እና በሐራጅ

 

ጫማዎች አልባሳት፣ የመኪና መለዋወጫ፣ የሞባይል ቀፎና አክሰሰሪ ኤሌክትሮኒክስ፣ ምግብ ነክ፣ የስፖርት እቃዎች፣ የእጅ ሰዓት፣ ኮስሞቲክስ መነፅር፣ ጌጣ ጌጦች፣ ጠፍታፋ ብረት፣ ላሜራ የወዳደቁ ብረቶችና ፕላስቲኮች እና ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎች

ለግልጽና ለሐራጅ ጨረታ 21/09/2018 እስከ ጠዋቱ 3:45

 

ለግልጽ ጨረታ 21/09/2018 . ከጠዋቱ 400 ሲሆን የሐራጅ ጨረታ የመጀመሪያ ጊዜ 21/09/2018 . 500 ሰዓት ይሆናል።

 

5. የጨረታ መክፈቻ ቦታ፡- በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።

6. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋሰትና ያስያዙት (cpo) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

7. ከአሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ3 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን በመረከብ ከመጋዝን ማውጣት ይኖርበታል።

8. ከላይ በተ.ቁ 7 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪ ያስያዙት ገንዘብ እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለኮሚሽኑ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።

9. ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

በጉምሩክ ኮሚሽን የአዋሽ ቅ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-29
  • Bid closing time: 11:00
  • Bid closing (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-05-29 11:00
  • Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Ethiopian Revenue & Customs Authority Awash Branch
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100 (መቶ) ብር
  • Published: May 22, 2026
  • Posted at: 2026-05-22T08:23:25.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders