የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ፍ/ቤት የቤት የሃራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ አውጥቷል

Description

ሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሃራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የአፈፃፀም ከሳሽ መ/ር እዮብ በጋሻው እና የአፈፃፀም ተከሳሽ ወ/ሮ በረከት ሲከበር መካከል ስላለው የባልናሚስት የአፈፃፀም ክርክር ጉዳይ በጋራ የነበራቸውን የመኖሪያ ቤትና ቦታ በውሳኔ መሰረት በአይነት መካፈል የማይቻል በመሆኑ በሞላሌ ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ ልዩ ስሙ ዞን 4 ተብሎ ከሚጠራው ስፍራ ከምስራቅ የሳምሶን ገብረህይዎት የቤት መስሪያ ቦታ ከምእራብ የወርቅነህ በሻህ ቤት እና ቦታ ከሰሜን የመኪና መንገድ ከደቡብ የስለሺ ገመቹ የቤት መስሪያ ቦታ መካከል የሚገኘውን የመኖሪያ ቤትና ቦታ ስፋቱ 200 ካሬ ሜትር በሆነ ቦታላይ የተሰራ 65 ቅጠል ቆርቆሮ የወሰደ ቤት እና 15 ቅጠል ቆርቆሮ የወሰደ ኩሽና ቤት ከነውሃ ቆጣሪው ይህንን ቤትና ቦታ ተጫራቾች ቀርበው ከፍተኛ ዋጋ ላቀረበ ተጫራች በግልፅ ጨረታ ስለሚሸጥ በ21/10/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት እስከ 6፡00 ሰአት ድረስ የመኖሪያ ቤትና ቦታው በሚገኝበት ቦታ ጨረታው ይካሄዳል፡፡ ይህንን ቤትና ቦታ በግልፅ ጨረታ መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች መግዛት ይችላል፡፡ የጨረታው አሸናፊ የሆነ አካል ያሸነፈበትን ገንዘብ 1/4ኛውን ወዲያውኑ የሚያሲዝ ሲሆን ቀሪውን 3/4ኛውን ደግሞ በ15 ቀን ውስጥ አሟልቶ የሚያቀርብ መሆኑን አውቀው መጫረት እና መግዛት የሚፈልግ በቦታው ተገኝተው መግዛት ይችላሉ።

ማሳሰቢያ፡- ፍ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ሃራጁን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስቁ 0919 842 755 መጠየቅ ይችላሉ።

የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ፍ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-28
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid opening: 2026-06-28 12:00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Menz Mama Meder Woreda Court
  • Published: May 22, 2026
  • Posted at: 2026-05-22T08:54:24.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders