የቤት ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት እነ አቶ ምንዳ አስራት እና በፍ/ባለዕዳ ወ/ሮ ተድባብ አበበ መካክል ስላለው የናርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.184148 በቀን 27/07/2015ዓ.ም እና የፌ/መ/ደ/ፍ/ ቤት በኮ/መ/ቁ.188754 በቀን 07/9/2015ዓ.ም እና በኮ/መ/ቁ.188754 በቀን 09/07/2018ዓ.ም በዋለው ችሎት በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 11 የቤት ቁጥር አዲስ የሆነ መኖሪያ ቤት 1ኛ ጣልቃ ገብ እና 2ኛ ጣልቃ ገብ ከሰሩት የግል ቤት ውስጥ ያለው የይዞታ ስፋት በካርታቸው 356ካ/ሜ ከፕላን አንጻር ሲረጋገጥ ከአጠቃላይ ይዞታ ላይ ተግባራዊ የሆነ 109 ካ/ሜ የሚቀነስ ቤቱ ለመኖሪያ የሚያገለግል ሲሆን አሁን ባለው ለድርጅት እያገለገለ ያለ 1ኛ ጣልቃ ገብ እና 2ኛ ጣልቃ ገብ ከሰሩት የግል ቤት ውጭ ያለው የውርስ ቤት ብቻ ቤቱና ቦታ በተመለከተ እስከ 2014 ዓ.ም በጀት አመት ግብር የተከፈለ ሲሆን የ2015ዓ.ም በጀት አመት በአዲስ ተመን አስተምኖ የሚከፈል ሲሆን ይዞታ በባዬ ወ/ጻዲቅ ስም ተመዝግቦ ይገኛል። የሐራጅ መነሻ 15,274,847.40 ( አስራ አምስት ሚሊየን ሁለት መቶ ሰባ አራት ሺህ ስምንት መቶ አርባ ሰባት ከ40/100) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሚያዚያ 28 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ ተይዞ በዕለቱ ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል። ስለሆነም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ 188754 በቀን 30/08/2018 ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ድጋሚ ሐራጅ ሆኖ 1/4ኛ 3,818.711.85 (ሶስት ሚሊዮን ስምንት መቶ አስራ ስምንት ሺህ ሰባት መቶ አስራ አንድ ከ85/100) ሆኖ የትራዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሰኔ 19 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ C.P.O የሚመጣ ተጫራች በጨረታው ኣይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤት/ስም C.P.O አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-26
- Bid closing time: 11:00
- Bid opening: 2026-06-26 11:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Court Judicial Procedure Directorate
- Bid bond: 25%
- Published: May 23, 2026
- Posted at: 2026-05-23T07:34:14.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.