221 ካ.ሜ የሆነ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት እነ ብስራት ፈቃዱ እና የፍ/ባለዕዳ እነታሪኳ ዳምጤ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/198798 20/2/2018 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ እና በኮ/መ/ቁ/207517 በ24/04/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ውስጥ የሚገኝ የቤት ቁጥር 9999/1 በተከሳሾች ስም የተመዘገበ ቤት እና ይዞታ የካርታ ቁጥር የካ/172463/04 የተመዘገበ የነበረ ካርታ በመቀየሩ የተነሳ ካርታው የተወገደ (Void) የተደረገ ሲሆን ካርታ ግን የነበረው ነው የቦታው ስፋት በጂ.አይ.ኤስ 1988 ዓ.ም ላይ በሚታየው የግቢው አጥር መሰረት 221 ካ.ሜ የሆነ ይዞታው በ67ኛ ዙር 12.60 ካ.ሜ የመንገድ ጥናት የሚቆርጠው ሆኖ ይዞታው አዋሶኞቹ በምስራቅ ሚኪያስ ሽፈራው በምዕራብ ወ/ሮ ዙፋን አሰፋ በሰሜን መንገድ በደቡብ አቶ ፋሲል ታደለ የሚያዋስኑት ሆኖ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 4,798,000 ( አራት ሚሊዮን ሰባት መቶ ዘጠና ስምንት ሺህ) ሆኖ የትራዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚያመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/ አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ አሠርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በሕጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም
ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-23
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-06-23 10:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published: May 23, 2026
- Posted at: 2026-05-23T07:40:15.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.