የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

በድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ  ማስታወቂያ

በፍ/ባለመብት እነ ቤተል ተፈራ እና በፍ/ባለዕዳ አቶ እንዳለ ተፈራ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ/193279 በሚያዝያ 24 ቀን 2017 ዓ.ም እና በኮ/መ/ቁ/204248 በ20/10/2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 6 የቤ.ቁ/123 በሟች ፶ አለቃ ተፈራ ወ/አማኑኤል ስም ተመዝግቦ የሚገኘውን ቤት ቤቱ ያረፈበት 79 ካ.ሜ በፕሮፖርሽን ከግቢው የሚደርሰው ለቤቱ የሚደርሰው የቦታ ስፋት 161 ካ.ሜ ጠቅላላ በፕሮፖርሽን የሚደርሰው የቦታው ስፋት 240 ካ/ሜ የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 15,123,920 (አስራ አምስት ሚሊዮን አንድ መቶ ሀያ ሦስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሀያ ብር) ሆኖ እንደሚሸጥ በጥቅምት 19 ቀን 2018 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል የሚል ማስታወቂያ ወጥቶ በዕለቱ ተጫራች አልቀረበም፡፡ ይህንኑ ለፍ/ቤቱ ሪፖርት ተደርጎ ፍ/ቤቱ በ3/3/2018 ዓ.ም በድጋሚ ጨረታ እንዲወጣ ትዕዛዝ የሰጠ በመሆኑ በሁለተኛ ጨረታ የሚያዘው 1/4ኛ ብር 3,780,980 (ሦስት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሰማኒያ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ብር) በማስያዝ መሳተፍ የሚቻል ሆኖ የትራንዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ለየካቲት 25 ቀን 2018 ዓ.ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ ተይዞ በዕለቱ ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል፡፡ ስለሆነም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.204248 በቀን 30/08/2018 ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ድጋሚ ሐራጅ ሆኖ መነሻው ከ0/ዜሮ/ሆኖ 1/4ኛ 3,780,980 (ሦስት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሰማኒያ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ብር) በማስያዝ መሳተፍ የሚቻል ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚያመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO  በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ አሠርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም

ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-24
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-06-24 10:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
  • Bid bond: 25%
  • Published: May 23, 2026
  • Posted at: 2026-05-23T07:45:12.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders