የግዮን ሆቴል ድርጅት በቅጥር ጊቢ ውስጥ የሚገኙ ለተለያዩ የንግድ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ ሱቆችን በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የግዮን ሆቴል ድርጅት በቅጥር ጊቢ ውስጥ የሚገኙ ለተለያዩ የንግድ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ ሱቆችን በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።

የተፈቀዱ የንግድ አይነቶች

  • ለካፌ እና ለሬስቶራንት
  • ለዲኮርና አበባ መሸጫ
  • ለውበት ሣሎን
  • ለሶቬኒር ሱቆች
  • ለባህል አልባሳት መሸጫ ሱቆች
  • ለተለያዩ ሱቆች እና ድርጅቱ ከሚሰጠው አገልግሎት ውጭ ለሆኑ የንግድ አይነቶች

ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።

  • ለሚሠሩት የንግድ ሥራ ኘሮፖዛል ማቅረብ፤
  • በዘርፉ ለሚሰማሩበት ሞያ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤
  • የንግድ ምዘገባ ሰርተፍኬት፤
  • የሚከራዩትን የንግድ ቤት ከተማ አስተዳደሩ በሚያወጣው ስታንዳርድ መሠረት የተጀመሩ የእድሳት ሥራውን በራሣቸው ወጪ ለማጠናቀቅ እና ለስድስት ወር ውል ለመግባት ፈቃደኛ የሆኑ፤
  • ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ለእያንዳንዱ ጨረታ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በዋናው እንግዳ መቀበያ በመክፈል ለእያንዳንዱ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከፋሲሊቲ መምሪያ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።
  • የጨረታው ሳጥን የጨረታ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ በወጣበት በ10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ጨረታው የሚከፈትበት የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
  • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 551 3222 Ext 5429/5163 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
  • የሥራ ሰዓት፡ ከሰኞ እስከ ሀሙስ ጠዋት 2፡00 – 6፡00 ከሰዓት 7፡00 – 11፡00 አርብ ጠዋት ከ2፡00 – 5፡30 ከሰዓት 7፡30 እስከ 11፡00
  • ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ለመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የግዮን ሆቴሎች ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-02
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ በወጣበት በ10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-02 12:00
  • Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ በወጣበት በ10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ghion Hotels Enterprise
  • Bid document price: ለእያንዳንዱ ጨረታ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/
  • Published: May 24, 2026
  • Posted at: 2026-05-25T11:33:42.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders