አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የሐራጅ ሽያጭ  ማስታወቂያ

አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸዉንና በሠንጠረዡ የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

  • ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼  (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በኣቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
  • የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል:: በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል። በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል።
  • ተበዳሪው /መያዣ ሰጪው/ በሐራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ። ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።
  • የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል፡፡ ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ለቀሪው የሊዝ ክፍያ ገዢው ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል። ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ወይም ማየት ይቻላል።
  • ከታች በሰኝጠረዥ ዉስጥ በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሰዉ ንብረት በሀራጅ ሊሸጥ በባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟላ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ /አሸናፊ/ ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል።
  • ከታች በሰንጠረዥ ዉስጥ በተራ ቁጥር 2 እና 3 የተጠቀጠቀሱት ንብረቶች በሀራጅ ሲሽጡ ለገዥዉ ከፊል ፋይናንስ/ብድር/ ባንካችን የማይሰጥ ስለሆነ በካሽ ክፍያ ብቻ ግብይቱ እንደሚፈፀም እንገልፃለን።
  • ከታች በሰኝጠረዥ ዉስጥ በተራ ቁጥር 3 የተጠቀሰዉ ንብረት ከኤስ.ዲ.ፒ (Spatial Development Plan) ፕላን ጋር ተነጻጽሮ ሲታይ የኮሪደር ልማት በግንባታ ላይ ያለዉን ህንጻ የማይነካ ሲሆን፤ የተገነባዉን መጋዘን ግን በስሜን ምዕራብ አቅጣጫ 3(ሶስት) ሜትር የሚነካዉ መሆኑን ከሸገር ከተማ ገላን ክ/ከተማ ፕላንና ልማት ጽ/ቤት የቀረበዉ መረጃ ያሳያል።
  •  የጨረታ ቦታ አዲስ አበባ ከተማ፤ ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ለገሀር በሚገኘው የአቢሲንያ ባንክ ኢማ ዋና መስሪያ ቤት 4ኛ ፎቅ ፎርክሎዠር እና ዴት ሊትጌሽን ለጨረታ ባዘጋጀዉ ቢሮ ላይ ነው።
  • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115 15 11 53 እና 0115 15 07 ኤአ በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
  • ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተ.ቁ

የተበዳሪው ስም

የመያዣ ሰጪው ስም

የንብረቱ አይነት እና አገልግሎት

የቦታዉ ስፋት በካ.ሜ

የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር

ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ

የጨረታው መነሻ ዋጋ በብር

ጨረታው የሚካሄድበት ቀን

የምዝገባ ሰዓት

የጨረታ ሰዓት

ጨረታ የወጣበት ጊዜ

1

አቶ ኢሳያስ ካሳዬ በቀለ

አቶ ተስፋዬ ቶላ ደሜ

G+1 መኖሪያ ቤት

 

160

 

BI/14922/09

 

ኦሮሚያ ብ/ክ/መንግስት ቢሾፍቱ ከተማ ቀበሌ 01

10,703,843.59

 

ሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም

 

4:30-5:30

 

5፡30-6፡00

ለመጀመሪያ ጊዜ

 

2

አቶ ይገረም ተፈረ አወቀ

አቶ ሰለሞንመኮንን አድማሱ እና ወይ ሠላማዊት ዮሴፍ

መኖሪያ ቤት

 

475

 

የካ/200985/09

 

አዲስ አበባ ከተማ በቀድሞ የካ ክ/ከተማ ወረዳ 12 (በአሁኑ ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 14)

8,413,484.13

 

ሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም

 

8:30-9:30

 

9:30-10:00

 

ለመጀመሪያ ጊዜ

 

3

ቤክፋም ጠቅላላ ንግድ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

አቶ በረከት

ክንፈ ባህታ

ግንባታው ያልተጠናቀቀ ለንግድ የሚሆን ህንጻና መጋዘን

2500

 

022622/1

 

በቀድሞ አዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 04 በአሁኑ ኦሮሚያ ብንመንግስት ሽገር ከተማ አስተዳደር ገላን ክ/ከተማ

28,233,809.58

 

ሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ.ም

 

4:30-5:30

 

5፡30-6፡00

በድጋሚ

 

አቶ በረከት ክንፈ ባህታ

 


Tender details

  • Deadline: 2026-07-01
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): የሐራጁ መዝጊያ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-07-01 12:00
  • Bid opening (note): የሐራጁ መክፈቻ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Bank of Abyssinia S.C.
  • Buyer address: Addis Ababa Ethiopia
  • Bid bond: 25%
  • Published: May 24, 2026
  • Posted at: 2026-05-25T12:39:07.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders